የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w07 6/15 ገጽ 31
  • የአንባቢያን ጥያቄዎች

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የአንባቢያን ጥያቄዎች
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2007
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • የአንባብያን ጥያቄዎች
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2001
  • የእባቡ ዘር፣ እንዴት ተጋለጠ?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1996
  • ሰይጣን ሔዋንን ለማነጋገር በእባብ የተጠቀመው ለምንድን ነው?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2011
  • የመጽሐፍ ቅዱስ አጠቃላይ ስምምነት
    መጽሐፍ ቅዱስ—የአምላክ ቃል ነው ወይስ የሰው?
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2007
w07 6/15 ገጽ 31

የአንባቢያን ጥያቄዎች

ሔዋንን ያነጋገራት እባብ እግሮች ነበሩት?

ዘፍጥረት 3:14 ላይ እንደተዘገበው በኤደን ገነት ሔዋንን ያሳታትን እባብ ይሖዋ አነጋግሮታል። አምላክ እንዲህ አለው:- “ይህን ስለ ሠራህ፣ ‘ከከብቶችና ከዱር እንስሳት ሁሉ ተለይተህ የተረገምህ ሁን፤ በሕይወትህ ዘመን ሁሉ፣ በደረትህ እየተሳብህ ትሄዳለህ፤ ዐፈርም ትበላለህ።’” መጽሐፍ ቅዱስ ሔዋንን ለማሳሳት ያገለገለው እንስሳ እርሷን ባነጋገረበት ጊዜ እግሮች እንደነበሩት የገለጸው ነገር የለም። የዘፍጥረት 3:14 አጻጻፍ አንዳንዶችን እንዲህ ብለው እንዲያስቡ ቢያደርጋቸውም፣ እባቦች ከዚህ እርግማን በፊት እግር ነበራቸው ብለን መደምደም አይኖርብንም። ለምን?

በመጀመሪያ ደረጃ ይሖዋ ፍርዱን ያስተላለፈው በእባቡ ላይ ሳይሆን ይህንን እንስሳ ለመጥፎ ተግባር በተጠቀመበት መንፈሳዊ ፍጡር ማለትም በሰይጣን ላይ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ ሰይጣንን ‘የሐሰት አባት’ እና ‘የጥንቱ እባብ’ በማለት ይጠራዋል። እነዚህ ሁለት መጠሪያዎች ሔዋን የአምላክን ትእዛዝ እንድትተላለፍ ለማድረግ ሰይጣን በሚታይ እንስሳ ይኸውም በእባብ እንደተጠቀመ ይጠቁሙናል።—ዮሐንስ 8:44፤ ራእይ 20:2

እባቦችን የፈጠራቸው አምላክ ነው፤ አዳም ደግሞ ስም ያወጣላቸው ሰይጣን ሔዋንን ለማሳት በእባብ ከመጠቀሙ በፊት ነው። ሔዋንን ያነጋገራት እባብ የማሰብና የማመዛዘን ችሎታ ስለሌለው ለተንኮል ድርጊቱ ተጠያቂ አይሆንም። እባቡ፣ ሰይጣን እየተጠቀመበት እንዳለ የማያውቅ ከመሆኑም ሌላ አምላክ በዓመጸኞቹ ላይ ያስተላለፈውን ፍርድ መረዳት አይችልም።

ታዲያ አምላክ እባቡን ‘በደረትህ ትሳባለህ’ ሲል የረገመው ለምንድን ነው? እባብ መሬት ለመሬት በደረቱ እየተሳበ፣ አፈር የሚልስ ይመስል ምላሱን ቶሎ ቶሎ የሚያወጣ መሆኑ ሰይጣን ያለበትን የተዋረደና ዝቅተኛ ሁኔታ ለመግለጽ ተስማሚ ምሳሌ ነው። ሰይጣን ቀደም ሲል ከፍ ያለ ቦታ የነበረው የአምላክ መልአክ ቢሆንም በአሁኑ ወቅት፣ መጽሐፍ ቅዱስ እንጦርጦስ ብሎ በሚጠራው መዋረድን በሚያመለክት ሁኔታ ውስጥ ይገኛል።—2 ጴጥሮስ 2:4 NW

በተጨማሪም፣ እባብ የሰውን ተረከዝ ሊያቆስል እንደሚችል ሁሉ የተዋረደው ሰይጣንም የአምላክን “ዘር” ‘ተረከዝ ይቀጠቅጣል።’ (ዘፍጥረት 3:15) የዚህ ዘር ዋነኛ ክፍል ኢየሱስ ክርስቶስ ሲሆን የሰይጣን ወኪሎች ጊዜያዊ ጉዳት አድርሰውበታል። የምሳሌያዊው እባብ ራስ ግን ውሎ አድሮ በክርስቶስና ትንሣኤ ባገኙት ቅቡዓን ባልንጀሮቹ አማካኝነት ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ይቀጠቀጣል። (ሮሜ 16:20) በመሆኑም አምላክ እባቡን መርገሙ፣ መንፈሳዊ ፍጡር የሆነው ‘የጥንቱ እባብ’ ማለትም ሰይጣን ዲያብሎስ እንደሚዋረድና በስተ መጨረሻም እንደሚጠፋ የሚያሳይ ተስማሚ ምሳሌ ነው።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ