የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w10 2/1 ገጽ 23
  • ይህን ያውቁ ኖሯል?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ይህን ያውቁ ኖሯል?
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2010
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ቢራ—ወርቃማው መጠጥ
    ንቁ!—2004
  • ለአልኮል መጠጦች ያለህ አመለካከት አምላካዊ ነውን?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1996
  • የአልኮል መጠጥ መጠጣት ስህተት ነው?
    ንቁ!—2006
  • የአልኰል መጠጦችን መውሰድ ይገባሃልን?
    ወጣትነትህን በተሻለ መንገድ ተጠቀምበት
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2010
w10 2/1 ገጽ 23

ይህን ያውቁ ኖሯል?

በጥንት ጊዜ ከወይን ጠጅ ሌላ ምን ሌሎች የአልኮል መጠጦች ይጠመቁ ነበር?

▪ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ “የወይን ጠጅ” እና “ብርቱ መጠጥ” የሚሉት አገላለጾች በብዙ ቦታዎች ላይ በአንድነት ተጠቅሰዋል። (ዘዳግም 14:26፤ ሉቃስ 1:15) የአልኮል መጠጦች የሚዘጋጁት ከወይን፣ ከቴምር፣ ከበለስ፣ ከፖም፣ ከሮማንና ከመሳሰሉ ፍራፍሬዎች ብቻ ሳይሆን ከማርም ይዘጋጅ ነበር።

እርግጥ ነው፣ “ብርቱ መጠጥ” የሚለው ሐረግ ቢራንም ሊያመለክት ይችላል። “ብርቱ መጠጥ” ተብሎ የተተረጎመው የዕብራይስጥ ቃል፣ በመስጴጦምያ ውስጥ ከተራ ገብስ የሚጠመቀውን ቢራ ከሚያመለክተው ከአካዲያን ቃል ጋር የተያያዘ ነው። ይህ መጠጥ የአልኮል ይዘቱ ትንሽ ቢሆንም ከመጠን በላይ ከተጠጣ ሊያሰክር ይችላል። (ምሳሌ 20:1) በጥንቷ ግብፅ መቃብሮች ውስጥ በሸክላ የተሠሩ የመጥመቂያ ናሙናዎችና የጠማቂ ምስሎች ተገኝተዋል። በባቢሎን በቤተ መንግሥቶችም ሆነ በድሆች ቤት ውስጥ ቢራ የሚዘወተር መጠጥ ነበር። ፍልስጥኤማውያንም ተመሳሳይ ቢራ ይጠጡ ነበር። አርኪኦሎጂስቶች በፓለስቲና ምድር ውስጥ በተለያዩ ቦታዎች ማጥለያ ያላቸው ደምበጃኖችን አግኝተዋል። እነዚህ ደምበጃኖች ማጥለያ ያላቸው መሆኑ ገፈቱን ለማጣራት ይረዳሉ፤ ይህ ደግሞ ሰዎች የተጣራ ቢራ እንዲጠጡ ያስችላቸዋል።

በሐዋርያው ጳውሎስ ዘመን በአንዳንድ ወቅቶች በመርከብ መጓዝ በጣም አደገኛ የነበረው ለምንድን ነው?

▪ ሐዋርያው ጳውሎስ ተሳፍሮባት የነበረች አንዲት መርከብ፣ ኃይለኛ አውሎ ነፋስ በመነሳቱ ምክንያት በትንሿ እስያ የባሕር ዳርቻ ጥግ ጥጉን ይዛ ወደ ምዕራብ አቅጣጫ ለመጓዝ ብዙ ጊዜ ወስዶባት ነበር። የመጽሐፍ ቅዱስ ዘገባ እንደሚናገረው አንድ ቦታ ላይ ሲደርሱ “የማስተሰረያ ቀን ጾም እንኳ ሳይቀር በማለፉ ወቅቱ የባሕር ላይ ጉዞ ለማድረግ አደገኛ” ሆኖ ነበር። ጳውሎስ አብረውት ይጓዙ ለነበሩ ሰዎች ጉዟቸውን ለመቀጠል ጥረት የሚያደርጉ ከሆነ “በጭነቱና በመርከቡ ላይ ብቻ ሳይሆን [በነፍሳቸው] ላይም እንኳ ሳይቀር ከፍተኛ ጉዳትና ጥፋት” ሊከተል እንደሚችል ገልጾላቸው ነበር።—የሐዋርያት ሥራ 27:4-10

የማስተሰረያ ቀን ጾም የሚውለው በመስከረም መጨረሻ ወይም በጥቅምት መጀመሪያ ላይ ነው። የሮም መርከበኞች የባሕር ላይ ጉዞ ለማድረግ አስተማማኝ የሚሆነው ከግንቦት 27 እስከ መስከረም 14 ያለው ጊዜ እንደሆነ ያውቁ ነበር። ከመስከረም 14 እስከ ኅዳር 11 ድረስ የባሕር ጉዞ ማድረግ አደገኛ ሲሆን ከኅዳር 11 እስከ መጋቢት 10 ባለው ጊዜ ውስጥ ደግሞ በባሕሩ ላይ መጓዝ ፈጽሞ የማይታሰብ ነገር ነበር። ከጳውሎስ ተሞክሮ መረዳት እንደሚቻለው ለዚህ አንደኛው ምክንያት የአየሩ ንብረት ተለዋዋጭ መሆኑ ነው። (የሐዋርያት ሥራ 27:13-44) መርከበኞች ኃይለኛ አውሎ ነፋስ እንዲሁም ጉዞውን አስቸጋሪ የሚያደርጉ የተለያዩ ሁኔታዎች ያጋጥሟቸው ነበር። ቀን ቀን ፀሐይ ማታ ማታ ደግሞ ከዋክብት በደመናው ይጋረዱ ነበር። በተጨማሪም ጭጋግና ዝናብ እይታን ስለሚጋርዱ መርከበኞች ፊት ለፊት ሊያጋጥሟቸው የሚችሉ አደገኛ ነገሮችን ከርቀት ማየት አስቸጋሪ ይሆንባቸዋል።

[በገጽ 23 ላይ የሚገኝ ሥዕል]

የግብፃውያንን የእንጨት የቢራ መያዣዎች የሚያሳዩ ናሙናዎች

[ምንጭ]

Erich Lessing/Art Resource, NY

[በገጽ 23 ላይ የሚገኝ ሥዕል]

የሮማውያን የጭነት መርከብ 100-200 ዓ.ም. ገደማ

[ምንጭ]

Pictorial Archive (Near Eastern History) Est.

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ