የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w11 2/1 ገጽ 3
  • እየፈረሰ ያለው ለምንድን ነው?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • እየፈረሰ ያለው ለምንድን ነው?
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2011
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ፍቅር በጠፋበት ትዳር ተጠምዶ መኖር
    ንቁ!—2001
  • ጋብቻ ማዕበሉን መቋቋም ይችል ይሆን?
    ንቁ!—2006
  • የይሖዋ ምሥክሮች ስለ ፍቺ ምን አመለካከት አላቸው?
    ስለ ይሖዋ ምሥክሮች ብዙ ጊዜ የሚነሱ ጥያቄዎች
  • አምላክ ላቋቋመው የጋብቻ ዝግጅት አክብሮት ይኑራችሁ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2018
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2011
w11 2/1 ገጽ 3

እየፈረሰ ያለው ለምንድን ነው?

“ፈሪሳውያንም ወደ [ኢየሱስ] መጥተው ሊፈትኑት በማሰብ ‘አንድ ሰው በማንኛውም ምክንያት ሚስቱን እንዲፈታ ሕግ ይፈቅድለታል?’ አሉት።”—ማቴዎስ 19:3

በኢየሱስ ዘመን የኖሩ አንዳንድ ሰዎች ‘ትዳር ዘላቂ መሆን አለበት? ደግሞስ ዘላቂ መሆን ይችላል?’ የሚሉት ጥያቄዎች አሳስበዋቸው ነበር። ኢየሱስ ለእነዚህ ሰዎች እንዲህ አላቸው፦ “ፈጣሪ ከመጀመሪያውም ወንድና ሴት አድርጎ እንደፈጠራቸው አላነበባችሁም? ‘በዚህ ምክንያት ሰው ከአባትና ከእናቱ ይለያል፤ ከሚስቱም ጋር ይጣበቃል፤ ሁለቱም አንድ ሥጋ ይሆናሉ’ ብሎ እንደተናገረስ አላነበባችሁም? በመሆኑም ከዚህ በኋላ አንድ ሥጋ ናቸው እንጂ ሁለት አይደሉም። ስለዚህ አምላክ ያጣመረውን ማንም ሰው አይለያየው።”a (ማቴዎስ 19:4-6) ከዚህ በግልጽ መመልከት እንደምንችለው አምላክ ትዳር ዘላቂ እንዲሆን ዓላማው ነበር።

በዛሬው ጊዜ በብዙ አገሮች 40 በመቶ ገደማ ወይም ከዚያ በላይ የሚሆኑ ባለትዳሮች በፍቺ ምክንያት ‘ይለያያሉ።’ ታዲያ መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ትዳር የሚሰጠው ምክር ጊዜ አልፎበታል ማለት ነው? ብዙ ትዳሮች የሚፈርሱት መጀመሪያውንም ዝግጅቱ ችግር ስላለበት ይሆን?

ይህን ለማስረዳት አንድ ምሳሌ እንመልከት፦ ሁለት ባልና ሚስት ተመሳሳይ የሆነ ቤት ገዙ እንበል። የመጀመሪያዎቹ ባልና ሚስት ቤታቸውን የሚያድሱት ከመሆኑም በላይ በጥንቃቄ ይዘውታል። በዚህም ምክንያት ቤቱ አልፈረሰም። ሌሎቹ ባልና ሚስት ግን ጊዜ ወስደው ቤታቸውን ለማሳደስም ሆነ በጥንቃቄ ለመያዝ ምንም ጥረት አላደረጉም። በመሆኑም ቤቱ ፈራርሶ ከጥቅም ውጪ ሆነ። ለሁለተኛው ቤት መፍረስ ምክንያቱ ምንድን ነው? የቤቱ አሠራር ወይስ የባለቤቶቹ አያያዝ? በዋነኝነት ተጠያቂ የሚሆኑት የቤቱ ባለቤቶች እንደሆኑ ግልጽ ነው።

በተመሳሳይም ብዙ ትዳሮች የሚፈርሱት የጋብቻ ተቋም ችግር ስላለበት አይደለም። ይህ ቢሆንማ በሚሊዮን የሚቆጠሩ የተሳኩ ትዳሮች ባልኖሩ ነበር። እንዲህ ዓይነቶቹ ትዳሮች ሰዎች በግለሰብ፣ በቤተሰብና በኅብረተሰብ ደረጃ ደስተኛና የተረጋጋ ሕይወት እንዲኖራቸው አስተዋጽኦ ያደርጋሉ። ይሁን እንጂ ትዳር ዘላቂ እንዲሆን ከተፈለገ ልክ እንደ ቤት ጥሩ እንክብካቤ ብሎም በየጊዜው እድሳት ሊደረግለት ይገባል።

ትዳራችሁ የቀናትም ሆነ የብዙ ዓመታት ዕድሜ ይኑረው መጽሐፍ ቅዱስ ትዳርን እንዴት መጠገንና ማጠናከር እንደሚቻል የሚሰጠውን ምክር በመከተል ጋብቻችሁን የተሳካ ማድረግ ትችላላችሁ። በዚህ ረገድ የተሳካላቸው አንዳንድ ባለትዳሮች ምን እንዳሉ በሚቀጥለው ርዕስ ላይ እንመልከት።

[የግርጌ ማስታወሻ]

a አንድ ሰው የትዳር ጓደኛውን መፍታት የሚችለው በፆታ ብልግና ምክንያት ብቻ እንደሆነ መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል።​—ማቴዎስ 19:9

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ