የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w12 4/1 ገጽ 16-17
  • ክርስቲያኖች የሚጠመቁት ለምንድን ነው?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ክርስቲያኖች የሚጠመቁት ለምንድን ነው?
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2012
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ጥምቀት—ትልቅ ቦታ የሚሰጠው ግብ!
    ለዘላለም በደስታ ኑር!—አሳታፊ የመጽሐፍ ቅዱስ መማሪያ
  • ለመጠመቅ ዝግጁ ነህ?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2020
  • የጥምቀትህ ትርጉም
    እውነተኛውን አንድ አምላክ አምልክ
  • የጥምቀትህ ትርጉም
    እውነተኛው አንድ አምላክ ያስገኘው የአምልኮ አንድነት
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2012
w12 4/1 ገጽ 16-17

ከአምላክ ቃል ተማር

ክርስቲያኖች የሚጠመቁት ለምንድን ነው?

ይህ ርዕስ በአእምሮህ ሊመላለሱ የሚችሉ ጥያቄዎችን በማንሳት መልሶቹን መጽሐፍ ቅዱስህ ውስጥ የት ቦታ ላይ ማግኘት እንደምትችል ይጠቁምሃል። የይሖዋ ምሥክሮች ለጥያቄዎቹ በተሰጡት መልሶች ላይ ከአንተ ጋር ለመወያየት ፈቃደኞች ናቸው።

1. የክርስቲያኖች ጥምቀት ምን ትርጉም አለው?

ጥምቀት ከአምላክ ጋር ጥሩ ዝምድና መመሥረት እንድንችል እሱን የምንጠይቅበት መንገድ ነው። ስለሆነም አንድ ክርስቲያን መጠመቅ ያለበት በሕፃንነቱ ሳይሆን ስለ አምላክ ማወቅ እና የክርስቶስ ደቀ መዝሙር መሆን በሚችልበት ዕድሜ ላይ ሲደርስ ነው። (የሐዋርያት ሥራ 8:12፤ 1 ጴጥሮስ 3:21) ኢየሱስ ያዘዛቸውን ነገሮች ስንማርና ተግባራዊ ስናደርግ የእሱ ደቀ መዝሙር እንሆናለን።​—ማቴዎስ 28:19, 20⁠ን አንብብ።

የኢየሱስ ሐዋርያት በነበሩበት ዘመን ብዙ ሰዎች ስለ አምላክ እና ስለ ኢየሱስ በተማሩት ነገር ላይ ተመሥርተው አፋጣኝ እርምጃ ወስደዋል። ለምሳሌ ያህል፣ በዚያ ወቅት ይኖር የነበረ አንድ ሰው የኢየሱስ ሞት ለመዳን በር እንደከፈተ ሲረዳ ወዲያውኑ ደቀ መዝሙር ሆኗል። በዛሬው ጊዜም ቅን ልብ ያላቸው በርካታ ሰዎች የኢየሱስ ተከታዮች ለመሆን መርጠዋል።​—የሐዋርያት ሥራ 8:26-31, 35-38⁠ን አንብብ።

2. ኢየሱስ የተጠመቀው ለምንድን ነው?

አጥማቂው ዮሐንስ፣ ኢየሱስን በዮርዳኖስ ወንዝ ውስጥ በማጥለቅ ሲያጠምቀው ኢየሱስ 30 ዓመቱ ነበር። የኢየሱስ ጥምቀት፣ አምላክ ለእሱ ያለውን ፈቃድ ለመፈጸም እንደወሰነ ያመለክት ነበር። (ዕብራውያን 10:7) ይህ ደግሞ ለሰው ልጆች ኃጢአት ሲል ሕይወቱን መሥዋዕት አድርጎ ለመስጠት ፈቃደኛ መሆንን ይጨምራል። ኢየሱስ በምድር ላይ ለመኖር ከሰማይ ከመውረዱ በፊትም ቢሆን ምንጊዜም አባቱን ይሖዋን ይወድደው እንዲሁም ይታዘዘው ነበር።​—ማርቆስ 1:9-11⁠ን፤ ዮሐንስ 8:29⁠ን እና ዮሐ 17:5⁠ን አንብብ።

3. አንድ ክርስቲያን መጠመቅ ያለበት ለምንድን ነው?

እኛ የሰው ልጆች ኃጢአተኞች ሆነን ስለተወለድን ያለንበት ሁኔታ ከኢየሱስ ይለያል። ያም ሆኖ የኢየሱስ መሥዋዕታዊ ሞት ከአምላክ ጋር ጥሩ ዝምድና ለመመሥረት እንድንችል መንገድ ከፍቶልናል። (ሮም 5:10, 12፤ 12:1, 2) እንዲያውም የአምላክ ቤተሰብ አባል መሆን እንችላለን። (2 ቆሮንቶስ 6:18) ይሁንና እንዲህ ዓይነት መብት ማግኘት የሚቻለው እንዴት ነው? በመጀመሪያ በሕይወታችን ሙሉ የአምላክን ፈቃድ ለማድረግ ቃል በመግባት በጸሎት አማካኝነት ራሳችንን ለይሖዋ መወሰን ያስፈልገናል። በዚህ መንገድ ራሳችንን ከወሰንን በኋላ ውሳኔያችንን ለሌሎች ለማሳወቅ በሕዝብ ፊት እንጠመቃለን።​—ማቴዎስ 16:24⁠ን እና 1 ጴጥሮስ 4:2⁠ን አንብብ።

4. ለጥምቀት መዘጋጀት የምትችለው እንዴት ነው?

የይሖዋ ምሥክሮች ወደ አምላክ መቅረብ ከሚፈልግ ከማንኛውም ሰው ጋር መጽሐፍ ቅዱስን ያጠናሉ። መጽሐፍ ቅዱስን ማጥናትና በክርስቲያናዊ ስብሰባዎች ላይ መገኘት ለአምላክ ያለህን ፍቅርና በእሱ ላይ ያለህን እምነት ያጠናክሩልሃል። በተጨማሪም አዎንታዊ አመለካከት እንዲኖርህና ጥሩ ልማዶችን እንድታዳብር ይረዱሃል። ፍቅርን፣ እምነትን እና ሌሎች አምላካዊ ባሕርያትን ማዳበርህ ይሖዋን ለዘላለም ለማገልገል የገባኸውን ቃል ጠብቀህ እንድትኖር ያስችልሃል።​—ዮሐንስ 17:3⁠ን እና ዕብራውያን 10:24, 25⁠ን አንብብ።

ተጨማሪ ማብራሪያ ለማግኘት በይሖዋ ምሥክሮች የተዘጋጀውን ትክክለኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ምንድን ነው? የተባለን መጽሐፍ ምዕራፍ 18 ተመልከት።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ