የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w12 9/1 ገጽ 22
  • ይህን ያውቁ ኖሯል?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ይህን ያውቁ ኖሯል?
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2012
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ይህን ያውቁ ኖሯል?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2012
  • ለአምላክ ሕዝብ ጥብቅና ቆማለች
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2011
  • ለአምላክ ሕዝብ ጥብቅና ቆማለች
    በእምነታቸው ምሰሏቸው
  • ይህን ያውቁ ኖሯል?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2022
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2012
w12 9/1 ገጽ 22

ይህን ያውቁ ኖሯል?

በጥንት ዘመን ደብዳቤዎች ይላኩ የነበረው እንዴት ነው?

ደብዳቤ የሚያመላልስ የፋርስ መልእክተኛ

ደብዳቤ የሚያመላልስ የፋርስ መልእክተኛ

በፋርስ፣ ከመንግሥት ወይም ከአገር ጉዳዮች ጋር የተያያዙ ደብዳቤዎችን የማድረስ ኃላፊነትን የሚወጣው የመንግሥት የፖስታ አገልግሎት ነበር። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሚገኘው የአስቴር መጽሐፍ በፋርስ ስለነበረው ስለዚህ ዓይነቱ የፖስታ አገልግሎት ሲናገር እንዲህ ይላል፦ “መርዶክዮስ ትእዛዙን በንጉሥ ጠረክሲስ ስም ጽፎ በንጉሡ የቀለበት ማኀተም አተመው፤ ከዚያም በተለይ ለንጉሡ በተገሩ ፈጣን ፈረሶች በሚጋልቡ መልእክተኞች እጅ ላከው።” (አስቴር 8:10) የሮም መንግሥትም ከአስተዳደርና ከወታደራዊ ጉዳዮች ጋር የተያያዙ ደብዳቤዎችን ለመላክ የሚጠቀመው በዚሁ መንገድ ነበር።

በሌላ በኩል ግን ሐዋርያው ጳውሎስም ሆነ ሌሎች ግለሰቦች፣ የጻፏቸውን የግል ደብዳቤዎች ለመላክ በሚፈልጉበት ወቅት ቀደም ሲል የተጠቀሰውን ዓይነት የፖስታ አገልግሎት ማግኘት አይችሉም ነበር። ደብዳቤውን የጻፈው ሰው ሀብታም ከሆነ መልእክቱን እንዲያደርስለት ባሪያውን መላክ ይችል ነበር። ይሁንና አብዛኞቹ ሰዎች ደብዳቤዎቻቸውን የሚልኩት ወደሚፈለገው ቦታ በሚሄዱ በሚያውቋቸው ሰዎች ወይም በማያውቋቸው መንገደኞች እጅ ነው። የቤተሰብ አባላት፣ ጓደኞች፣ ወታደሮች ወይም ነጋዴዎች ደብዳቤውን ይዘው ሊሄዱ ይችላሉ። በዚህ ወቅት አሳሳቢው ነገር ደብዳቤውን የሚያደርሰው ሰው እምነት የሚጣልበት መሆን አለመሆኑ እንዲሁም ደብዳቤው ምንም ሳይሆን ለተላከለት ግለሰብ በጥንቃቄ መድረስ መቻሉ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚናገረው ጳውሎስ አንዳንድ ደብዳቤዎቹን እንዲያደርሱለት የእምነት ባልንጀሮቹን ይልክ ነበር።—ኤፌሶን 6:21, 22፤ ቆላስይስ 4:7

በጥንቷ እስራኤል የንግድ ልውውጥ ይካሄድ የነበረው እንዴት ነው?

የፍራፍሬ ገበያ የሚያሳይ ምስል

የፍራፍሬ ገበያን የሚያሳይ ምስል

የብሔሩ ኢኮኖሚ በዋነኝነት የተመሠረተው በእርሻ፣ በከብት እርባታና በንግድ ላይ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ በከተማይቱ በሮች ስለሚገኙ የገበያ ቦታዎች ይጠቅሳል፤ ከእነዚህ የገበያ ቦታዎች መካከል “የበጎች በር”፣ ‘የዓሣ በር’ እና ‘የገል በር’ የተባሉት ይገኙበታል። (ነህምያ 3:1, 3፤ ኤርምያስ 19:2) እነዚህ ስሞች በቦታው የሚሸጠውን ነገር የሚያመለክቱ ይመስላል። በተጨማሪም ቅዱሳን መጻሕፍት፣ ‘የእንጀራ ጋጋሪዎች ሰፈር’ ስለሚባለው አካባቢ እንዲሁም ለገበያ ስለሚቀርቡ የተለያዩ ሸቀጦች ይጠቅሳሉ።—ኤርምያስ 37:21

የሸቀጦቹን ዋጋ በተመለከተስ ምን ማለት ይቻላል? በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ ትንታኔ የሚሰጥ አንድ መጽሐፍ እንዲህ ብሏል፦ “የሸቀጦች ዋጋ በየጊዜው ስለሚለዋወጥ አንድ ሸቀጥ በአንድ ወቅት በሆነ ቦታ ላይ ይሸጥ የነበረበትን ትክክለኛ ዋጋ ማወቅ ያስቸግራል።” ያም ሆኖ መጽሐፍ ቅዱስን ጨምሮ በጥንት ዘመን የተዘጋጁ አንዳንድ የመረጃ ምንጮች እንደሚያሳዩት በጥንት ጊዜም እንኳ የዋጋ ግሽበት ነበረ። ለምሳሌ ያህል በድሮ ጊዜ የባሪያ ንግድ በጣም የተለመደ ነገር ነበር። ዮሴፍ የተሸጠው በ20 ጥሬ ብር (ሰቅል ሊሆን ይችላል) ነው፤ በ18ኛው መቶ ዘመን ዓ.ዓ. አንድ ባሪያ ይሸጥ የነበረው በዚህ ዋጋ ሊሆን ይችላል። (ዘፍጥረት 37:28) ከሦስት መቶ ዓመታት በኋላ የአንድ ባሪያ ዋጋ 30 የብር ሰቅል ነበር። (ዘፀአት 21:32) በስምንተኛው መቶ ዘመን ዓ.ዓ. ይኸው ዋጋ ወደ 50 ሰቅል ከፍ ብሏል። (2 ነገሥት 15:20 NW) ከሁለት መቶ ዓመታት በኋላ ማለትም ፋርስ የዓለም ኃያል መንግሥት በነበረበት ወቅት ዋጋው 90 ሰቅል ወይም ከዚያ በላይ ሆኖ ነበር። ከዚህ ማየት እንደሚቻለው የዋጋ ንረት በዘመናችን ብቻ ያለ ችግር አይደለም።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ