የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w13 3/1 ገጽ 16
  • የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2013
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ኢየሱስ የአምላክ ልጅ ተብሎ የተጠራው ለምንድን ነው?
    የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
  • አምላክ ኢየሱስን ወደ ምድር የላከው ለምንድን ነው?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2012
  • ኢየሱስ ክርስቶስ ማን ነው?
    ትክክለኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ምንድን ነው?
  • በእርግጥ ኢየሱስ የአምላክ ልጅ ነው?
    ንቁ!—2006
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2013
w13 3/1 ገጽ 16
[በገጽ 16 ላይ የሚገኝ ሥዕል]

የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው

ኢየሱስ የአምላክ ልጅ የተባለው ለምንድን ነው?

አምላክ ቃል በቃል ልጆች የምትወልድለት ሚስት የለውም። እሱ ሕይወት ያላቸው ነገሮች በሙሉ ፈጣሪ ነው። ሰዎች የተፈጠሩት የአምላክን ባሕርያት ማንጸባረቅ እንዲችሉ ተደርገው ነው። በመሆኑም አምላክ የፈጠረው የመጀመሪያው ሰው ማለትም አዳም “የአምላክ ልጅ” ተብሎ ተጠርቷል። በተመሳሳይም ኢየሱስ የአባቱ ዓይነት ባሕርያት እንዲኖሩት ተደርጎ ስለተፈጠረ “የአምላክ ልጅ” ተብሏል።—ሉቃስ 3:38⁠ን እና ዮሐንስ 1:14, 49⁠ን አንብብ።

ኢየሱስ የተፈጠረው መቼ ነው?

አምላክ ኢየሱስን የፈጠረው አዳምን ከመፍጠሩ በፊት ነው። እንዲያውም አምላክ ኢየሱስን ከፈጠረው በኋላ መላእክትን ጨምሮ ሌሎች ነገሮችን በሙሉ ለመሥራት በእሱ ተጠቅሟል። መጽሐፍ ቅዱስ ኢየሱስን የአምላክ “ፍጥረት ሁሉ በኩር” በማለት የሚጠራው ለዚህ ነው።—ቆላስይስ 1:15, 16⁠ን አንብብ።

ኢየሱስ በቤተልሔም ከመወለዱ በፊት በሰማይ መንፈሳዊ ፍጡር ሆኖ ይኖር ነበር። ጊዜው ሲደርስ ኢየሱስ ሰው ሆኖ መወለድ እንዲችል አምላክ ከሰማይ ወደ ማርያም ማኅፀን አዛወረው።—ሉቃስ 1:30-32⁠ን፣ ዮሐንስ 6:38⁠ን እና 8:23⁠ን አንብብ።

አምላክ፣ ኢየሱስ ሰው ሆኖ በምድር ላይ እንዲወለድ ያደረገው ለምንድን ነው? ኢየሱስ የፈጸመው ልዩ ተልእኮስ ምንድን ነው? የእነዚህን ጥያቄዎች መልስ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ማግኘት የምትችል ሲሆን መልሶቹም አምላክና ኢየሱስ ስላደረጉልህ ነገር ያለህ እውቀትና አድናቆት እንዲጨምር ያደርጋሉ።

ተጨማሪ ማብራሪያ ለማግኘት በይሖዋ ምሥክሮች የተዘጋጀውን የዚህን መጽሐፍ ምዕራፍ 4 ተመልከት

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ