የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w14 7/1 ገጽ 16
  • መጸለይ ያለብን ለምንድን ነው?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • መጸለይ ያለብን ለምንድን ነው?
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2014
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • በጸሎት አማካኝነት ከአምላክ ጋር መቀራረብ
    አምላክ ከእኛ የሚፈልገው ምንድን ነው?
  • ወደ አምላክ የመጸለይ ውድ መብት
    መጽሐፍ ቅዱስ ምን ያስተምረናል?
  • በጸሎት አማካኝነት ወደ አምላክ ቅረብ
    ለዘላለም በደስታ ኑር!—አሳታፊ የመጽሐፍ ቅዱስ መማሪያ
  • በጸሎት አማካኝነት ከአምላክ ጋር ያለህን ዝምድና አጠናክር
    ትክክለኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ምንድን ነው?
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2014
w14 7/1 ገጽ 16
አንድ አረጋዊ ሲጸልዩ

የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው

መጸለይ ያለብን ለምንድን ነው?

ይሖዋ አምላክ ስለሚያሳስቡን ነገሮች በነፃነት ሁልጊዜ እንድንነግረው ይፈልጋል። (ሉቃስ 18:1-7) ስለሚያስብልን ስንጸልይ ይሰማናል። ታዲያ የሰማዩ አባታችን እንድንጸልይ በደግነት እስከጋበዘን ድረስ ግብዣውን የማንቀበልበት ምን ምክንያት ይኖራል?—ፊልጵስዩስ 4:6⁠ን አንብብ።

የምንጸልየው ከአምላክ እርዳታ ለመጠየቅ ብቻ አይደለም። ጸሎት ወደ አምላክ እንድንቀርብም ይረዳናል። (መዝሙር 8:3, 4) የሚሰማንን ነገር ሁሉ አዘውትረን ለአምላክ የምንገልጽለት ከሆነ ወደ እሱ ይበልጥ እንቀርባለን።—ያዕቆብ 4:8⁠ን አንብብ።

መጸለይ ያለብን እንዴት ነው?

አምላክ በምንጸልይበት ጊዜ የተራቀቁ ቃላትን እንድንጠቀም ወይም የተሸመደዱ ጸሎቶችን እንድንደግም አይፈልግም። አሊያም ደግሞ ስንጸልይ የተለየ ዓይነት አኳኋን ወይም አቋቋም እንዲኖረን አይጠብቅብንም። ይሖዋ የሚፈልገው ከልብ የመነጨ ጸሎት እንድናቀርብ ነው። (ማቴዎስ 6:7) ለምሳሌ ያህል፣ በጥንቷ እስራኤል የነበረችው ሐና በቤተሰቧ ውስጥ ስላጋጠማት ከባድ ችግር ጸልያ ነበር። በኋላም የሚያስጨንቃት ነገር ተወግዶ ምኞቷ ሲሳካ ከልብ በመነጨ ጸሎት አምላክን አመስግናለች።—1 ሳሙኤል 1:10, 12, 13, 26, 27⁠ን እና 1 ሳሙ 2:1⁠ን አንብብ።

ጸሎት እንዴት ያለ ግሩም መብት ነው! ስለሚያሳስቡን ነገሮች ወደ ፈጣሪ መጸለይ እንችላለን። በተጨማሪም ልናወድሰውና ለሚያደርግልን ነገር ሁሉ ልናመሰግነው እንችላለን። በእርግጥም እንዲህ ዓይነቱን ውድ መብት ፈጽሞ ችላ ልንለው አይገባም።—መዝሙር 145:14-16⁠ን አንብብ።

ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት በይሖዋ ምሥክሮች የተዘጋጀውን ትክክለኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ምንድን ነው? የተባለውን መጽሐፍ ምዕራፍ 17 ተመልከት

www.jw.org/am ላይም ይገኛል

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ