የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w15 10/1 ገጽ 4
  • ጸሎቴን የሚሰማ አለ?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ጸሎቴን የሚሰማ አለ?
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2015
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • በጸሎት አማካኝነት ከአምላክ ጋር ያለህን ዝምድና አጠናክር
    ትክክለኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ምንድን ነው?
  • አምላክ ጸሎታችንን ይሰማል?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (ለሕዝብ የሚሰራጭ)—2021
  • ወደ አምላክ የመጸለይ ውድ መብት
    መጽሐፍ ቅዱስ ምን ያስተምረናል?
  • በጸሎት እርዳታ ማግኘት የሚቻለው እንዴት ነው?
    በምድር ላይ በገነት ለዘላለም መኖር ትችላለህ
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2015
w15 10/1 ገጽ 4
ደቀ መዛሙርቱ አቀርቅረው ሳለ ኢየሱስ ቀና ብሎ ሲጸልይ

የሽፋኑ ርዕሰ ጉዳይ | መጸለይ የሚያስገኘው ጥቅም አለ?

ጸሎቴን የሚሰማ አለ?

አንዳንድ ሰዎች ጸሎታቸውን የሚሰማ ስለሌለ መጸለይ ጊዜ ማባከን እንደሆነ ያስባሉ። ሌሎች ደግሞ የሚጸልዩ ቢሆንም ምንም መልስ እንዳላገኙ ይሰማቸዋል። ለምሳሌ በአምላክ የማያምን አንድ ሰው፣ አምላክ እንዲህ ይመስላል ብሎ አንድ አካል በምናቡ ከፈጠረ በኋላ “እስቲ በሹክሹክታ እንኳ አናግረኝ” ብሎ ጸለየ። ከዚያ በኋላ ግን ከአምላክ “ምንም መልስ እንዳላገኘ” ተናግሯል።

ይሁንና መጽሐፍ ቅዱስ ጸሎት የሚሰማ አንድ አምላክ መኖሩን በማያሻማ መንገድ ይናገራል። መጽሐፍ ቅዱስ በጥንት ዘመን ለኖረ ሕዝብ የተነገረውን ይህን ሐሳብ ይዟል፦ “እርዳታ ለማግኘት በምትጮኹበት ጊዜ በእርግጥ ሞገስ ያሳያችኋል፤ ጩኸታችሁን እንደሰማም ይመልስላችኋል።” (ኢሳይያስ 30:19) ሌላ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ ደግሞ ‘የቅኖች ጸሎት ደስ ያሰኘዋል’ ይላል።—ምሳሌ 15:8

ኢየሱስ ወደ አባቱ ያቀረበው ጸሎት “ተሰማለት።”—ዕብራውያን 5:7

በተጨማሪም መጽሐፍ ቅዱስ ላቀረቡት ጸሎት መልስ ስላገኙ ሰዎች ይናገራል። አንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ ኢየሱስ ‘ከሞት ሊያድነው ለሚችለው ልመና’ እንዳቀረበ ከመግለጹም ሌላ ‘ጸሎቱ እንደተሰማለት’ ይናገራል። (ዕብራውያን 5:7) በዳንኤል 9:21 እና በ2 ዜና መዋዕል 7:1 ላይ ሌሎች ምሳሌዎችን እናገኛለን።

ታዲያ አንዳንድ ሰዎች ጸሎታቸው መልስ እንዳላገኘ የሚሰማቸው ለምንድን ነው? ጸሎታችን እንዲሰማልን ከፈለግን ወደ ማንኛውም አምላክ ወይም ወደ ቅዱሳን ሳይሆን የመጽሐፍ ቅዱስ አምላክ ወደሆነው ወደ ይሖዋa ብቻ መጸለይ ይኖርብናል። በተጨማሪም አምላክ፣ በእሱ ዘንድ ተቀባይነት ያላቸውን ነገሮች “ከፈቃዱ ጋር በሚስማማ ሁኔታ” እንድንጠይቅ ይፈልጋል። በዚህ መንገድ የምንጸልይ ከሆነ አምላክ ‘እንደሚሰማን’ ተናግሯል። (1 ዮሐንስ 5:14) ስለዚህ ጸሎታችን እንዲሰማልን ከፈለግን መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተገለጸውን አምላክ ማወቅና የእሱን ፈቃድ መማር ያስፈልገናል።

ብዙ ሰዎች፣ ጸሎት አንድ ዓይነት ሃይማኖታዊ ሥርዓት ብቻ እንዳልሆነና አምላክ ለእሱ የሚቀርበውን ጸሎት ሰምቶ መልስ እንደሚሰጥ ያምናሉ። በኬንያ የሚኖረው አይሳክ እንዲህ ብሏል፦ “መጽሐፍ ቅዱስ እንዲገባኝ እርዳታ ለማግኘት ጸልዬ ነበር። ከዚያ ብዙም ሳይቆይ አንድ ሰው ወዳለሁበት መጥቶ ስፈልገው የነበረውን እርዳታ ሰጠኝ።” በፊሊፒንስ የምትኖረው ሂልዳ ሲጋራ ማጨስ ለማቆም ትፈልግ ነበር። ብዙ ጊዜ ሊሳካላት ስላልቻለ ባለቤቷ “አምላክ እንዲረዳሽ ለምን አትጸልይም?” የሚል ሐሳብ አቀረበላት። እሷም ምክሩን በሥራ ላይ ካዋለች በኋላ እንዲህ ብላለች፦ “አምላክ ያደረገልኝ እርዳታ በጣም አስገርሞኛል። የማጨስ ፍላጎቴ እየጠፋ መጣ። ከዚያም ሙሉ በሙሉ ማጨስ አቆምኩ።”

አምላክ በግል የሚያሳስቡህ ነገሮች ከፈቃዱ ጋር የሚስማሙ እስከሆኑ ድረስ አንተን የመርዳት ፍላጎት አለው?

a መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚናገረው የአምላክ የግል ስም ይሖዋ ነው።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ