የርዕስ ማውጫ
ጥር 2016
© 2016 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
ከየካቲት 29, 2016–መጋቢት 6, 2016 ባለው ሳምንት
የ2016 የዓመት ጥቅሳችን ምንድን ነው? ዓመቱን ሙሉ ይህን ጥቅስ ስንመለከት በየትኞቹ ነጥቦች ላይ ልናሰላስል ይገባል? ይህ ርዕስ ከዓመት ጥቅሳችን የተሟላ ጥቅም ማግኘት የምንችለው እንዴት እንደሆነ ያብራራል።
ከመጋቢት 7-13, 2016 ባለው ሳምንት
12 ‘በቃላት ሊገለጽ የማይችለው የአምላክ ነፃ ስጦታ’ ግድ ይበላችሁ
ሐዋርያው ጳውሎስ እንደገለጸው ይሖዋ ‘በቃላት ሊገለጽ የማይችል ነፃ ስጦታ’ ሰጥቶናል። (2 ቆሮ. 9:15) ይህ ስጦታ ምንድን ነው? የክርስቶስ ኢየሱስን ፈለግ እንድንከተል፣ ወንድሞቻችንን እንድንወድና ሌሎችን ከልብ ይቅር እንድንል ግድ የሚለንስ እንዴት ነው? ይህ ርዕስ ለእነዚህ ጥያቄዎች መልስ የሚሰጥ ከመሆኑም ሌላ በመታሰቢያው በዓል ሰሞን ልናደርጋቸው የሚገቡ አንዳንድ ጠቃሚ ነገሮችን ያብራራል።
ከመጋቢት 14-20, 2016 ባለው ሳምንት
ከመጋቢት 21-27, 2016 ባለው ሳምንት
እነዚህ ሁለት ርዕሶች አንድ ሰው ሰማያዊ ጥሪ እንዳለው የሚያውቀው እንዴት እንደሆነ እንዲሁም ግለሰቡ ከቅቡዓን አንዱ ሲሆን ምን እንደሚሰማው ያብራራሉ። በተጨማሪም ቅቡዓን ለራሳቸው ምን አመለካከት ሊኖራቸው እንደሚገባ እንዲሁም በዓለም ዙሪያ ከቂጣውና ከወይን ጠጁ የሚካፈሉት ሰዎች ቁጥር መጨመሩ ሊያሳስበን የማይገባው ለምን እንደሆነ እንመለከታለን።
ከመጋቢት 28, 2016–ሚያዝያ 3, 2016
28 ከአምላክ ጋር አብሮ መሥራት—አስደሳች መብት
ይሖዋ ዓላማውን ዳር በማድረስ ረገድ አገልጋዮቹ ከእሱ ጋር አብረው እንዲሠሩ ከጥንትም ጀምሮ ይጋብዛቸው ነበር። በዓለም ዙሪያ ምሥራቹ እንዲሰበክ የሚፈልግ ሲሆን እኛም በዚህ ሥራ እንድንካፈል ጋብዞናል። ይህ ርዕስ ከአምላክ ጋር አብረን መሥራታችን የሚያስገኝልንን በረከቶች ያብራራል።
ሽፋኑ
ማዳጋስካር
አንድ አቅኚ በሞሮንዳቫ፣ ማዳጋስካር አሊ ኦቭ ዘ ባኦባብ በተባለው ጎዳና ላይ ለአንድ ባለ ጋሪ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ ሲያነብለት
አስፋፊዎች
29,963
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች
77,984
በመታሰቢያው በዓል ላይ የተገኙ