ኢየሱስ የተሠቃየውና የሞተው ለምንድን ነው?
ቁጥር 2 2016
የኢየሱስ ሞት መታሰቢያ | ረቡዕ፣ መጋቢት 14, 2008 ዓ.ም. (መጋቢት 23, 2016)
© 2016 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
ይህ መጽሔት ማለትም መጠበቂያ ግንብ፣ የአጽናፈ ዓለም ገዢ የሆነውን ይሖዋ አምላክን ከፍ ከፍ ያደርጋል። በሰማይ ያለው የአምላክ መንግሥት በቅርቡ ክፋትን ሁሉ በማጥፋት ምድርን ወደ ገነትነት እንደሚለውጥ የሚገልጸውን ምሥራች በማብሰር ሰዎችን ያጽናናል። እኛ የዘላለም ሕይወት እንድናገኝ ሲል በሞተውና በአሁኑ ጊዜ የአምላክ መንግሥት ንጉሥ ሆኖ በመግዛት ላይ በሚገኘው በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ እምነት እንዲኖረን ያበረታታል። ይህ መጽሔት ከ1879 ጀምሮ ያለማቋረጥ ሲታተም የቆየ ሲሆን ከፖለቲካ ጉዳዮች ነፃ ነው። ትምህርቱ ሙሉ በሙሉ የተመሠረተው በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ ነው።
ይህ ጽሑፍ የሚሸጥ አይደለም። መጽሔቱ በዓለም አቀፍ ደረጃ መጽሐፍ ቅዱስን ለማስተማር ከሚታተሙት ጽሑፎች መካከል አንዱ ሲሆን ይህ የማስተማር ሥራ የሚደገፈው ደግሞ ሰዎች በፈቃደኝነት በሚያደርጉት መዋጮ ነው።
መዋጮ ለማድረግ www.jw.org/amን ይመልከቱ።
ሌላ መግለጫ ካልተሰጠ በቀር በመጽሔቱ ላይ የተጠቀሱት ጥቅሶች የተወሰዱት በዘመናዊ ቋንቋ ከተዘጋጀው አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ ነው።