የርዕስ ማውጫ
ከነሐሴ 28, 2017–መስከረም 3, 2017 ባለው ሳምንት
ይህ ርዕስ፣ ያለንን ቁሳዊ ሀብት በሰማይ ‘ወዳጆች ለማፍራት’ ልንጠቀምበት የምንችለው እንዴት እንደሆነ ያብራራል። (ሉቃስ 16:9) በተጨማሪም ስግብግብ ለሆነው የንግድ ሥርዓት ባሪያ ላለመሆን እንዲሁም ይሖዋን አቅማችን በፈቀደ መጠን ለማገልገል ምን ማድረግ እንደምንችል ይገልጻል።
ከመስከረም 4-10, 2017 ባለው ሳምንት
አንድ ክርስቲያን፣ የሚወደውን ሰው በሞት ማጣቱ ያስከተለበትን ሐዘን መቋቋም የሚችለው እንዴት ነው? ይሖዋ በኢየሱስ ክርስቶስ፣ በቅዱሳን መጻሕፍትና በክርስቲያን ጉባኤ አማካኝነት እንዲህ ላለው ሰው የሚያስፈልገውን መጽናኛ ይሰጠዋል። ይህ ርዕስ ሐዘን የደረሰባቸውን ማጽናናትም ሆነ እኛ ራሳችን መጽናኛ ማግኘት የምንችለው እንዴት እንደሆነ ያብራራል።
ከመስከረም 11-17, 2017 ባለው ሳምንት
መዝሙር 147 የአምላክ ሕዝቦች ይሖዋን እንዲያወድሱ በተደጋጋሚ ያበረታታል። መዝሙራዊው፣ አምላክን ለማወደስ እንዲነሳሳ ያደረገው ምንድን ነው? ይህ ርዕስ መዝሙራዊው አምላክን ለማወደስ ያነሳሳውን ምክንያት የሚያብራራ ከመሆኑም ሌላ እኛም አምላካችንን ማወደስ ያለብን ለምን እንደሆነ ይገልጻል።
ከመስከረም 18-24, 2017 ባለው ሳምንት
በርካታ ወጣት ወንድሞችና እህቶች በሙሉ ጊዜ አገልግሎት በቅንዓት እየተካፈሉ ነው። አንተስ በዚህ መስክ መሰማራት ትፈልጋለህ? ይህ ርዕስ፣ የወደፊት ሕይወትህ አስደሳችና ስኬታማ እንዲሆን የሚረዳ ዕቅድ ለማውጣት የሚያግዝህ ቅዱስ ጽሑፋዊ ምክር ይሰጣል።