የርዕስ ማውጫ
ከሰኔ 4-10, 2018 ባለው ሳምንት
ከሰኔ 11-17, 2018 ባለው ሳምንት
በዓለም ዙሪያ ያሉ ሰዎች የበለጠ ነፃነት ለማግኘት ጥረት ሲያደርጉ ይታያል። ክርስቲያኖች ነፃነት ስለ ማግኘት ምን አመለካከት ሊኖራቸው ይገባል? እውነተኛ ነፃነት የሚባለው ምን እንደሆነ፣ ይህን ነፃነት እንዴት ማግኘት እንደምንችል እንዲሁም ያለንን አንጻራዊ ነፃነት ራሳችንንም ሆነ ሌሎችን በሚጠቅም መንገድ ልንጠቀምበት የምንችለው እንዴት እንደሆነ በእነዚህ ሁለት ርዕሶች ላይ እንመለከታለን። ከሁሉ በላይ ደግሞ የእውነተኛ ነፃነት አምላክ የሆነውን ይሖዋን ማክበር የምንችለው እንዴት እንደሆነ እንማራለን።
ከሰኔ 18-24, 2018 ባለው ሳምንት
15 ማበረታቻ በመስጠት ረገድ ግሩም ምሳሌ የሆነውን ይሖዋን ምሰሉ
ከሰኔ 25, 2018–ሐምሌ 1, 2018 ባለው ሳምንት
እነዚህ ርዕሶች ይሖዋ ከጥንት ዘመን ጀምሮ አገልጋዮቹን ሲያበረታታ እንደቆየና አገልጋዮቹም የእሱን ምሳሌ እንደተከተሉ ያሳያሉ። በተጨማሪም እርስ በርስ ለመበረታታት የምናደርገውን ጥረት ከምንጊዜውም ይበልጥ ማጠናከራችን አስፈላጊ የሆነው ለምን እንደሆነ ያብራራሉ።
ከሐምሌ 2-8, 2018 ባለው ሳምንት
25 እናንት ወጣቶች፣ ትኩረታችሁ ያረፈው በመንፈሳዊ ግቦች ላይ ነው?
በጉባኤ ውስጥ ያሉ ወጣቶች፣ ይሖዋን በማስደሰት ላይ ትኩረት ካደረጉ የተሻለ ሕይወት መምራት ይችላሉ። ይህ ርዕስ ከልጅነት ጀምሮ መንፈሳዊ ግቦች ማውጣትና ለስብከቱ ሥራ ቅድሚያ መስጠት አስፈላጊ የሆነበትን ምክንያት ያብራራል።