የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 2/93 ገጽ 2
  • “ለቤዛው አድናቆት ማሳየት

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • “ለቤዛው አድናቆት ማሳየት
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—1993
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ለቤዛው አድናቆት ማሳየታችሁን ቀጥሉ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2021
  • ቤዛው—ከሁሉ የላቀ የአምላክ ስጦታ
    መጽሐፍ ቅዱስ ምን ያስተምረናል?
  • ቤዛው—ከሁሉ የላቀ የአምላክ ስጦታ
    ትክክለኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ምንድን ነው?
  • ቤዛው—ከአባታችን የተገኘ “ፍጹም ገጸ በረከት”
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2017
ለተጨማሪ መረጃ
የመንግሥት አገልግሎታችን—1993
km 2/93 ገጽ 2

“ለቤዛው አድናቆት ማሳየት

1 አንድ የሞተ ወዳጅ ወይም ዘመድ ተወዳጅ የነበረ መሆኑን የማሳየት ፍላጎት በሁሉም ባሕሎች ዘንድ የተለመደ ነው። በተለይ ያ ወዳጃችን የሞተው የሌሎችን ሕይወት ለማዳን ሲል ከሆነ አድናቆት ለማሳየት ያለን ፍላጎት ሊጠነክር ይችላል። የዘላለም ሕይወት የማግኘት ተስፋ ያላቸው ሁሉ ሚያዝያ 6 በሚከበረው የክርስቶስ ሞት መታሰቢያ በዓል ላይ በመገኘት ለቤዛው አድንቆት ለማሳየት ከሁሉ የበለጠ ምክንያት አላቸው። — 2 ቆሮ. 5:14፤ 1 ዮሐ. 2:2

2 የይሖዋን ፍቅር አድንቁ፦ ቤዛውን ላዘጋጀልን ለታላቁ በጎ አድራጊ ለይሖዋ አምላክ ጥልቅ አድናቆት ማሳየታችን እንዴት ተገቢ ነው! (1 ዮሐ. 4:9, 10) በሚልዮን ከሚቆጠሩት ጻድቃን መላእክት አንዱን ሳይሆን በከፍተኛ ሁኔታ ተወዳጅ የሆነውን አንድያ ልጁን ቤዛችን እንዲሆን ሲል ልዩ ስጦታ አድርጎ በመስጠቱ የይሖዋ ፍቅር ምን ያህል ጥልቅ እንደሆነ ተገልጿል። (ምሳሌ 8:22, 30) ይሖዋን ከማንም የበለጠ የሚያውቀው ይህ ልጁ ኢየሱስ ክርስቶስ “በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና” ሲል አሳስቦናል። — ዮሐንስ 3:16

3 የኢየሱስ ክርስቶስን ፍቅር አድንቁ፦ በተመሳሳይም ለብዙዎች ቤዛ ለመሆን ሲል ነፍሱን ለሰጠን ለኢየሱስ ክርስቶስ ጥልቅ አድናቆት ማሳየታችን ተገቢ ነው። (ማቴ. 20:28) ከቤዛው ጋር በተያያዘ ሁኔታ ለይሖዋ ፈቃድ በውዴታው በመታዘዙ ፍቅሩን ገልጿል። ለኛ ቤዛ ለመሆን ሲል ከአባቱና ስፍር ቁጥር ከሌላቸው መላእክት ጋር አብሮ እያለ የነበረውን ያን ሁሉ ምቹ ሁኔታ እንደተወ አስቡ። ኃጢአተኛ በሆኑ ሰዎች መካከል የመኖርና ለነሱ ተገዢ የመሆኑ ፈታኝ ሁኔታም ሆነ ቤዛውን ማቅረብ ማለት መሞትን የሚጠይቅ መሆኑን ማወቁ ፍቅሩን ከማሳየት አላገደውም። ከዚህ ይልቅ “የባሪያን መልክ ይዞ በሰውም ምሳሌ ሆኖ . . . ራሱን አዋረደ፣ ለሞትም ይኸውም የመስቀል ሞት [በመከራ እንጨት ላይ ለመሞት አዓት] እንኳ የታዘዘ ሆነ።” — ፊል. 2:5–8

4 ለቤዛው ያለንን አድናቆት የምናሳየው እንዴት ነው? ለቤዛው የሚኖረን አድናቆት እንዲሁ አመሰግናለሁ ከማለት አልፎ የሚሄድ መሆን ይኖርበታል። በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ስለተደረገው የአምላክ የመዳን ዝግጅት መማር ያስፈልገናል። (ዮሐንስ 17:3) ከዚያም በቤዛው ላይ እምነት እንዲኖረን ማድረግ አለብን። (ሥራ 3:19) በኋላም ራሳችንን በመወሰንና በመጠመቅ ራሳችንን ለይሖዋ ለመስጠት ከውስጥ መገፋፋት አለብን። (ማቴ. 16:24) ራሳችንን እንደወሰንን ሆነን በመኖር ለመዳን ሲባል ስለተዘጋጀው ስለዚህ አስደናቂ ቤዛ ለሌሎች ለመንገር የሚያስችለንን አጋጣሚ ሁሉ መዋጀት ይኖርብናል። — ሮሜ 10:10

5 እነዚህን ብቃቶች ማሟላት ከማንኛችንም አቅም በላይ የሆነ ነገር አይደለም። ሚክያስ 6:8 እንዲህ በማለት ያረጋግጥልናል:- “እግዚአብሔር [ይሖዋ አዓት] ከአንተ ዘንድ የሚሻው ምንድር ነው? ፍርድን [ፍትህን አዓት] ታደርግ ዘንድ፣ ምሕረትንም [ፍቅራዊ ደግነትን አዓት] ትወድድ ዘንድ፣ ከአምላክህም ጋር በትሕትና [ቦታህን ጠብቀህ አዓት] ትሄድ ዘንድ አይደለምን?” በተመሳሳይም ዳዊት ለይሖዋ እንዲህ ብሏል:- “ሁሉ ከአንተ ዘንድ ነውና፣ ከእጅህም የተቀበልነውን ሰጥተንሃልና።” — 1 ዜና. 29:14

6 ለአስደናቂው የይሖዋ ዝግጅት ያላችሁን አድናቆት ጥልቅ ለማድረግ ከመታሰቢያው በዓል ቀን በፊት ታላቁ ሰው የተባለውን መጽሐፍ ከምዕራፍ 112 እስከ 126 ለምን በቤተሰብ መልክ አታነቡትም? በዚህ መንገድ ሁላችንም ለቤዛው ያለንን አድናቆት ለማሳየት ሚያዝያ 6 ቀን 1993 ለሚከበረው የመታሰቢያው በዓል አእምሮአችንን ለማዘጋጀት እንችላለን።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ