የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 1/94 ገጽ 3-7
  • ማስታወቂያዎች

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ማስታወቂያዎች
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—1994
የመንግሥት አገልግሎታችን—1994
km 1/94 ገጽ 3-7

ማስታወቂያዎች

◼ የሚበረከቱ ጽሑፎች በጥር፦ ቀለሙ እየደበዘዘ ወይም እየለቀቀ በሚሄድ ወረቀት የታተሙ ወይም ከ1980 በፊት የታተሙ ማናቸውንም ባለ 192 ገጽ መጻሕፍት ማበርከት ይቻላል። እነዚህ መጻሕፍት የሌሏቸው ጉባኤዎች የሰው ልጅ አምላክን ለማግኘት ያደረገው ፍለጋ የተባለውን የእንግሊዝኛ መጽሐፍ ማበርከት ይችላሉ። በየካቲት፦ በምድር ላይ በገነት ለዘላለም መኖር ትችላለህ። በመጋቢት፦ ራእይ — ታላቁ መደምደሚያው ደርሷል! በሚያዝያና በግንቦት፦ መጠበቂያ ግንብ እና ንቁ! እንዲሁም (ትምህርት ቤት ከተባለው በስተቀር) ማናቸውንም ብሮሹር። ፍላጎት ያሳየ ሰው ከተገኘ ተመላልሶ መጠየቅ በሚደረግበት ጊዜ ኮንትራት እንዲገባ መጠየቅ ይቻላል። ማሳሰቢያ:- ከላይ የተጠቀሱት የዘመቻ ጽሑፎች የሚያስፈልጓቸው ጉባኤዎች በሚቀጥለው ወር በሚልኩት ወርኃዊ የጽሑፍ መጠየቂያ ቅጽ (S–14–AM) ላይ ማመልከት ይችላሉ። በጥር ወር ለሚደረገው የጽሑፍ ማበረከት ዘመቻ የሚሆኑ የቆዩ ጽሑፎች በቅርንጫፍ ቢሮው ወይም በተለያዩ የጽሑፍ ማከማቻ ቦታዎች ማግኘት ይቻላል። ሆኖም ጉባኤዎች ባሏቸው ጽሑፎች መጠቀም አለባቸው።

◼ ጉባኤዎች በዚህ ዓመት ቅዳሜ መጋቢት 26, 1994 ፀሐይ ከጠለቀች በኋላ ለሚከበረው የመታሰቢያው በዓል አመቺ የሆኑ ዝግጅቶች ማድረግ ይኖርባቸዋል። እያንዳንዱ ጉባኤ ራሱን ችሎ የመታሰቢያውን በዓል ቢያከብር የሚመረጥ ቢሆንም ሁልጊዜ እንዲህ ማድረግ አይቻል ይሆናል። በአንድ የመንግሥት አዳራሽ በርካታ ጉባኤዎች የሚጠቀሙ ከሆነ አንድ ወይም ከዚያ በላይ የሆኑ ጉባኤዎች ለዚያ ምሽት ሌላ መሰብሰቢያ ቦታ ቢፈልጉ የተሻለ ነው። ፍላጎት ያሳዩ አዳዲስ ሰዎች በበዓሉ ላይ ለመገኘት እንዳይቸግራቸው የመታሰቢያው በዓል የሚጀመረው በጣም ከመሸ በኋላ መሆን የለበትም። ከዚህም በላይ ከበዓሉ በፊት ወይም በኋላ ከአዲሶች ጋር ሰላምታ ለመለዋወጥ፣ ለአንዳንዶች ቀጣይ የሆነ መንፈሳዊ ድጋፍ ለመስጠት የሚያስችሉ ዝግጅቶችን ለማድረግ ወይም እዚያ የተገኙት ሁሉ እርስ በርስ ማበረታቻ ለመለዋወጥ እንዳይችሉ እስኪያደርጋቸው ድረስ ፕሮግራሙ በጣም የተጣበበ መሆን የለበትም። ሽማግሌዎች ሁሉንም ነገር በደንብ ካጤኑ በኋላ በመታሰቢያው በዓል ላይ የሚገኙት ሁሉ በአጋጣሚው ሙሉ በሙሉ መጠቀም እንዲችሉ ምን ዝግጅት ቢያደርጉ የተሻለ እንደሚሆን መወሰን ይኖርባቸዋል።

◼ ከየካቲት ጀምሮ (ከመጋቢት 6 ሳያልፍ) የክልል የበላይ ተመልካቾች መስጠት የሚጀምሩት አዲስ የሕዝብ ንግግር ርዕስ “የሰብዓዊ ፍጡራን መቃተት የሚያበቃው መቼ ይሆን?” የሚል ይሆናል።

◼ በ1994 በመታሰቢያው በዓል አካባቢ እንዲቀርብ የተዘጋጀው ልዩ የሕዝብ ንግግር በዓለም ዙሪያ እሁድ ሚያዝያ 10 ይሰጣል። የንግግሩ ርዕስ “ሃይማኖት ሰብዓዊው ኅብረተሰብ የሚጠብቅበትን ሳያደርግ ቀርቷልን?” የሚል ይሆናል። አስተዋጽዖው ይላክላችኋል። በዚያ የሳምንቱ መጨረሻ ላይ የክልል የበላይ ተመልካች ጉብኝት፣ የክልል ስብሰባ ወይም የልዩ ስብሰባ ቀን የሚኖራቸው ጉባኤዎች ልዩ ንግግሩን ከዚያ በሚቀጥለው ሳምንት ያደርጋሉ። ማንኛውም ጉባኤ ልዩ ንግግሩን ከሚያዝያ 10 በፊት ማድረግ የለበትም።

◼ ማኅበሩ ከ1960 እስከ 1969 ድረስ ያሉትን የእንግሊዝኛ መጠበቂያ ግንብ ጥራዞች (ባውንድ ቮልዩምስ) ማተም ጀምሯል። ጽሑፎቹን በማንኛውም ጊዜ ማግኘት ይቻላል። እነዚህን ጥራዞች የሚፈልግ ሁሉ በጉባኤው በኩል ማዘዝ ይችላል። እነዚህ ጥራዞች በልዩ ትዕዛዝ የሚገኙ መሆናቸውን እባካችሁ አስታውሱ።

◼ የአማርኛው ንቁ! ተዘጋጅቷል። የሚፈልጉትን መጠን ያዘዙ ጉባኤዎች በዚያው መሠረት ያገኛሉ። ያላዘዙ ግን የሚላክላቸው ብዛት አነስተኛ ይሆናል። ዋጋው ለአስፋፊዎች 0. 60 ለአቅኚዎች 0. 30

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ