የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 8/94 ገጽ 1
  • አዎንታዊ አመለካከት ያዙ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • አዎንታዊ አመለካከት ያዙ
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—1994
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • አዎንታዊ አመለካከት አዳብሩ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2004
  • ለአገልግሎታችሁ አዎንታዊ አመለካከት ይኑራችሁ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2021
  • የክርስቶስን አስተሳሰብ አንጸባርቁ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2000
  • በትዕግሥት የመጠበቅ ዝንባሌ ይኑራችሁ!
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2000
ለተጨማሪ መረጃ
የመንግሥት አገልግሎታችን—1994
km 8/94 ገጽ 1

አዎንታዊ አመለካከት ያዙ

1 በብዙ አገሮች ስለሚደረጉት አስደናቂ ጭማሪዎች ስናነብ እንዴት ደስ ይለናል! ይሁንና በአንዳንድ አካባቢዎች የመንግሥቱ አስፋፊዎች ለስብከቱ ሥራችን ቀዝቃዛ ስሜት ያላቸው፣ ግዴለሽ የሆኑ ሰዎች ወይም ቀጥተኛ ተቃውሞም ጭምር በተደጋጋሚ እንደሚያጋጥማቸው እንገነዘባለን። በክልላችን ውስጥ ያለው ሁኔታ ይህን የመሰለ ከሆነ አዎንታዊ አመለካከት መያዝ የምንችለው እንዴት ነው? ደቀ መዛሙርት በማድረጉ ሥራ የምናገኘውን ደስታ የሚነጥቀንን ወይም ቅንዓታችንን የሚያቀዘቅዝብንን አፍራሽ አስተሳሰብ ልንከላከለው የምንችለው እንዴት ነው?

2 አዎንታዊ አመለካከት ሚዛናችንን እንድንጠብቅ ይረዳናል። ፈታኝ ሁኔታዎች በሚያጋጥሙበትም ጊዜ እንኳን አፍራሽ አስተሳሰቦች በአመለካከታችን ላይ ተጽዕኖ እንዲያሳድሩ መፍቀድ የለብንም። ኢየሱስ ፍጹም ምሳሌ ትቶልናል። ትምህርቱን የተቀበሉት ካልተቀበሉት ጋር ሲወዳደሩ በጣም ጥቂት ነበሩ። ብዙዎች በትምህርቱ ተሰናክለዋል። ጽናቱን ክፉኛ የተፈታተኑት ችግሮች ገጥመውታል። ሃይማኖታዊ መሪዎች ሥራውን በመንቀፍ ሊገድሉትም አሲረዋል። ተተፍቶበታል፣ በጥፊ ተመቷል፣ ተዘብቶበታል፣ ተደብድቧል፣ በመጨረሻም ተገድሏል። ይሁንና በሠራው ሥራ ተደስቷል። ለምን? የአምላክን ፈቃድ የማድረግን አስፈላጊነት ተገንዝቦ ነበር፤ ተስፋ ቆርጦ ሥራውንም አላቆመም። — ዮሐ. 4:34፤ 13:17፤ ዕብ. 12:2

3 ለአገልግሎታችን ምን ጊዜም ትክክለኛ አመለካከት ይኑረን፦ ይህን ለማድረግ በአእምሮአችን ልንይዛቸው የሚገቡ ሁለት ወይም ሦስት ነገሮች አሉ። የያዝነውን መልእክት አብዛኞቹ ሰዎች እንደማይቀበሉት ወይም እንደሚቃወሙት አስታውሱ። (ማቴ. 13:14, 15) ምንም እንኳ ሐዋርያት በኢየሱስ ስም ማስተማራቸውን እንዲያቆሙ በግልጽ ቢታዘዙም፣ ለስብከት ተልእኳቸው ታማኝ ሆነው በመቆማቸው መከሩ መሰብሰቡን ቀጥሏል። (ሥራ 5:28, 29፤ 6:7) በአንዳንድ የአገልገሎት ክልሎች ውስጥ ከሌላው ጋር ስናወዳድረው ጆሯቸውን የሚሰጡን ሰዎች ቁጥር ጥቂት እንደሚሆን ከወዲሁ ማወቅ እንችላለን። (ማቴ. 7:14) ስለዚህ በአገልግሎት ክልላችን ውስጥ አንድ ሰው ብቻ እንኳን ቢሰማን የምንደሰትበት ምክንያት አለን። ደግሞም ተቃዋሚዎችም ጭምር የመስማት አጋጣሚ ማግኘት እንዳለባቸው አስታውሱ። (ሕዝ. 33:8) ውሎ አድሮ አንዳንድ ተቃዋሚዎች ተለውጠው የይሖዋ አምላኪዎች ይሆናሉ። የሚያዳምጡን ጥቂቶችም ቢሆኑ እንኳ ተገቢውን አመለካከት ከያዝን አገልግሎታችን የእርካታ ስሜት ሊያመጣልን ይችላል። ስለ አምላክ መንግሥት የሚናገረውን መልእክት ይዘን ወደ ሰዎች ቤት መሄዳችን ራሱ ምሥክርነት ነው። — ሕዝ. 2:4, 5

4 አዎንታዊ አመለካከት ለመያዝ የሚያበቁ ጥሩ ምክንያቶች አሉን። የዓለም አቀፉ ሥራ መደርጀትና ታላቁ መከራ እንደ ቀረበ የሚያሳዩት ምልክቶች ከዕለት ወደ ዕለት እየጨመሩ መሄዳቸው ለአምላክ ያደርን ሆነን በማገልገል ሁላችንም የተቻለንን እንድናደርግ ሊያንቀሳቅሱን ይገባል። (2 ጴጥ. 3:11, 14) በነሐሴ ወር የምናደርገው ቅንዓት የተሞላበት አገልግሎት ለተማርናቸው ነገሮች ያለንን አድናቆት የምንገልጽበት ጥሩ መንገድ ይሆናል። በቅርቡ ከጉባኤው ጋር መተባበር የጀመሩት አዳዲሶችም ጭምር የተማሩትን በተግባር በማዋል አዎንታዊ አመለካከት እንዲያሳዩ እንፈልጋለን። አንዳንዶቹ የመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪዎቻችን ያልተጠመቁ አስፋፊዎች ወደመሆን ደረጃ ደርሰው ከሆነ የነሐሴ ወር እነርሱን አገልግሎት ለማስጀመር በጣም አመቺ ጊዜ ሊሆንልን ይችላል።

5 አስፋፊዎችም ሆንን አቅኚዎች ሁላችንም ይሖዋ ከአቅማችን በላይ እንደማይጠይቅብን በማስታወሳችን እንጠቀማለን። (1 ዮሐ. 5:3) እንደሚደግፈን ቃል ገብቶልናል። (ዕብ. 13:5, 6) ሰዎች ግዴለሽ፣ ቀዝቃዛ ስሜት ያላቸው ወይም ተቃዋሚዎች ቢሆኑም እኛ አዎንታዊ አመለካከት ይዘን በስብከቱ መቀጠል አለብን፤ ምክንያቱም እንዲህ ማድረጋችን የአምላክ ፈቃድ ነው። — 1 ጢሞ. 2:3, 4

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ