ቲኦክራሲያዊ ዜናዎች
ሩዋንዳ፦ በሩዋንዳ ኪጋሊ ውስጥ ከፍተኛ የተሰብሳቢ ቁጥር ያላቸው ሦስት ጉባኤዎች እንደገና እየተንቀሳቀሱ ነው። በኪጋሊም ሆነ በዛየር ጎማ ከተማ ውስጥ የወንድሞቻችንን ችግር ለማቃለል የእርዳታ ኮሚቴ ተቋቁሟል። በጦርነቱ ወቅት ከ400 የሚበልጡ ወንድሞችን፣ ፍላጎት ያሳዩ ሰዎችንና ልጆቻውን በማጣታችን አዝነናል፤ ይሁን እንጂ በሰፈራ ጣቢያዎች ያሉ ወንድሞቻችን በአስተዳደር አካል ቅንጅት በተደረጉ ጥረቶች ከልዩ ልዩ አገሮች አስፈላጊውን ምግብ፣ መጠለያ፣ ብርድ ልብሶች፣ አልባሳትና መድኃኒት አግኝተዋል። የትርጉም ክፍሉም ለጥቂት ጊዜ ካቋረጠ በኋላ አስፈላጊውን መንፈሳዊ ምግብ ለወንድሞቻችን ማቅረቡን ቀጥሏል።