ቲኦክራሲያዊ ዜናዎች
አልባኒያ፦ በሐምሌ 353 የሚሆን አዲስ ከፍተኛ የአስፋፊዎች ቁጥር ላይ ተደርሷል፤ መጽሔት በማበርከትም በኩል ከፍተኛ ጭማሪ ተገኝቷል። የጉባኤ አስፋፊዎች በአማካይ 22.4 ሰዓት ያገለገሉ ሲሆን 1,073 የቤት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶችን መርተዋል።
ካሜሩን፦ በሐምሌ አዲስ ቅርንጫፍ ቢሮ መሠራቱ ከተገኘው 21,323 የደረሰ አዲስ ከፍተኛ የአስፋፊዎች ቁጥር ጋር ተገጣጥሟል።
ኢትዮጵያ፦ ስብሰባውን ለማስቀረት ጥረት ቢደረግም “አምላካዊ ፍርሃት” የተባለው የወረዳ ስብሰባ በአዲስ አበባ ከተማ ስታዲየም ተካሂዶ ከፍተኛ የተሰብሳቢዎች ቁጥር 9,360 ሲሆን 457 ሰዎች ተጠምቀዋል።
ዛየር፦ በብዙ መቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ስደተኞች ወደ ዛየር በመፍለሳቸው ምክንያት አስከፊ ሁኔታ ቢያጋጥማቸውም በሐምሌ 83,442 የደረሰ አዲስ ከፍተኛ የአስፋፊዎች ቁጥር ተገኝቷል። ወንድሞች እርስ በርስ ለመረዳዳት ከፍተኛ ጥረት ያደረጉ ሲሆን ከውጭ ለተላኩት እርዳታዎች ከፍተኛ አድናቆት እንዳሳዩ ተናግረዋል።