የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 1/95 ገጽ 7
  • ማስታወቂያዎች

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ማስታወቂያዎች
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—1995
የመንግሥት አገልግሎታችን—1995
km 1/95 ገጽ 7

ማስታወቂያዎች

◼ የምንጠቀምባቸው ጽሑፎች በጥር፦ ጉባኤው ያሉትን ከ1982 በፊት የታተሙ ማናቸውም ባለ 192 ገጽ መጻሕፍት። የቆዩ መጻሕፍት የሌሏቸው ጉባኤዎች ታላቁን አስተማሪ ማዳመጥ (በአማርኛ) ወይም የአምላክ ዘላለማዊ ዓላማ የተባለውን የእንግሊዝኛ መጽሐፍ ሊያበረክቱ ይችላሉ። በየካቲትና በመጋቢት፦ በምድር ላይ በገነት ለዘላለም መኖር ትችላለህ የተባለው መጽሐፍ ይበረከታል። ይህ መጽሐፍ ከተበረከተ በኋላ ተመላልሶ መጠየቅ ሊደረግ ይገባል፤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶችን ለማስጀመርም ጥረት መደረግ አለበት። በሚያዝያና በግንቦት፦ መጠበቂያ ግንብ እና ንቁ! መጽሔቶች። በተደጋጋሚ በተሸፈኑ የአገልግሎት ክልሎች ማንኛውንም ብሮሹር (ትምህርት ቤት ከተባለው ብሮሹር በስተቀር) ልንጠቀም እንችላለን። በተመላልሶ መጠየቅ ወቅት ፍላጎት ያሳዩ ሰዎችን ኮንትራት ልናስገባ እንችላለን። ማሳሰቢያ፦ ከላይ የተጠቀሱትን የዘመቻ ጽሑፎች እስካሁን ያልጠየቁ ጉባኤዎች በቀጣዩ ወር የጽሑፍ ማዘዣ ቅጽ (S–14 AM) መጠየቅ አለባቸው።

◼ ጉባኤዎች በዚህ ዓመት ዓርብ ሚያዝያ 14 ፀሐይ ከጠለቀች በኋላ ለሚከበረው የመታሰቢያው በዓል አመቺ የሆኑ ዝግጅቶች ማድረግ አለባቸው። እያንዳንዱ ጉባኤ ራሱን ችሎ የመታሰቢያውን በዓል ቢያክበር የሚመረጥ ቢሆንም ሁልጊዜ እንዲህ ማድረግ አይቻል ይሆናል። በአንድ የመንግሥት አዳራሽ ከአንድ በላይ ጉባኤዎች የሚጠቀሙ ከሆነ ምናልባት አንድ ወይም ከዚያ በላይ የሆኑ ጉባኤዎች ለዚያ ምሽት የሚሆን ሌላ መሰብሰቢያ ቦታ ማግኘት ይችሉ ይሆናል። ፍላጎት ያሳዩ አዳዲስ ሰዎች በበዓሉ ላይ ለመገኘት እንዳይቸገሩ የመታሰቢያው በዓል የሚጀምረው በጣም ከመሸ በኋላ መሆን የለበትም። ከዚህም በላይ ከበዓሉ በፊት ወይም በኋላ ከአዲሶች ጋር ሰላምታ ለመለዋወጥ፣ ለአንዳንዶች ቀጣይ የሆነ መንፈሳዊ ድጋፍ ለመስጠት የሚያስችሉ ዝግጅቶችን ለማድረግ ወይም እዚያ የተገኙት ሁሉ እርስ በርስ ማበረታቻ ለመለዋወጥ እንዳይችሉ እስኪያደርጋቸው ድረስ ፕሮግራሙ በጣም የተጣበበ መሆን የለበትም። ሽማግሌዎች ሁሉንም ነገር በደንብ ካጤኑ በኋላ በመታሰቢያው በዓል ላይ የሚገኙት ሁሉ በአጋጣሚው ሙሉ በሙሉ መጠቀም እንዲችሉ ምን ዝግጀት ቢያደርጉ የተሻለ እንደሚሆን መወሰን አለ ባቸው።

◼ እሑድ ሚያዝያ 23, 1995 በሁሉም ጉባኤዎች ልዩ የሕዝብ ንግግር ይሰጣል። የንግግሩ ርዕስ “የሐሰት ኃይማኖት ጥፋት ተቃርቧል” የሚል ይሆናል። በዚህ ዓመት በመታሰቢያው በዓል ላይ የሚገኙትን በሙሉ መጋበዛችሁን አረጋግጡ። የቤት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት እየተመራላቸው ያሉትን በሚልዮን የሚቆጠሩ ሰዎች ለመርዳት ልዩ ጥረት ይደረጋል። በዚያን ቀን ከሚደረገው ስብሰባ በኋላ የሚሰጠው መግለጫ አንድን ለልዩ ዓላማ የተዘጋጀ ትራክት በማሰራጨቱ ተግባር እንዲሳተፉ እነሱንና ወንድሞቻችንን በቅድሚያ ያዘጋጃቸዋል። ከዚህም ጋር መግለጫው ግለሰቦች የሚያጋጥሟቸውን ችግሮችና ከአምላክ ቃል ጋር ለመስማማት ቁርጥ ያለ እርምጃ የመውሰድን አስፈላጊነት የሚጠቁም ይሆናል።

◼ ከመጋቢት ጀምሮ የክልል የበላይ ተመልካቾች መስጠት የሚጀምሩት አዲስ የሕዝብ ንግግር “መለኮታዊ ትምህርት በዓለም አቀፍ ደረጃ ድል ይቀዳጃል” የሚል ይሆናል። ይህም በ1993 እና በ1994 የአገልግሎት ዓመት የተደረጉትን “መለኮታዊ ትምህርት” የተሰኙ ልዩ የብሔራት አቀፍ ስብሰባዎችን የሚያጎላ በስላይድ የሚቀርብ ትምህርት ይሆናል። ንግግሩ እስከሚቀርብበት ቀን ድረስ ስላይዶቹን ላላገኙ ጉባኤዎች የክልል የበላይ ተመልካቾች “በመጽናናት ሁሉ አምላክ ተማመኑ” የሚል ርዕስ ያለውን ንግግር ያቀርባሉ፤ ስላይዶቹን እስኪያገኙ ድረስም ይህንኑ ንግግር ማቅረባቸውን ይቀጥላሉ። ሁሉም ጉባኤዎች በስላይድ አማካኝነት የሚቀርበው ንግግር ከተደረገላቸው በኋላ በ1996 መጀመሪያ ላይ የሚወጣው በክልል የበላይ ተመልካች የሚሰጠው አዲስ የሕዝብ ንግግር ፕሮግራም እስኪወጣ ድረስ የክልል የበላይ ተመልካቾች “በመጽናናት ሁሉ አምላክ ተማመኑ” የሚል ርዕስ ያለውን ንግግር ማቅረባቸውን ይቀጥላሉ።

◼ በጥር 9 በሚጀምረው ሳምንት የአገልግሎት ስብሳባ ላይ የሚገኙ የተጠመቁ አስፋፊዎች በሙሉ በቅድሚያ የተሰጠ የሕክምና መመሪያ/የሕክምና ባለሙያዎችን ከኃላፊነት ነፃ የሚያደርገው ሰነድ እና የመታወቂያ ካርድ የተባሉት ካርዶች የግል ቅጂ እንዲደርሳቸው ይደረጋል።

◼ ልዩ የአገልግሎት ክልል የምንሸፍንበት የሚቀጥለው ዘመቻ ከመጋቢት እስከ ግንቦት ባሉት ወራት እንዲደረግ ታቅዷል። ልዩ አቅኚ በመሆን ለማገልገል የሚፈልጉ የዘወትር አቅኚዎች ስማቸውን፣ ነጠላ ወይም ባለትዳር መሆናቸውን፣ ዕድሜያቸውን፣ የተጠመቁበትን ቀን፣ ከተጠቀሱት ውስጥ በየትኞቹ ወራት ማገልገል እንደሚችሉና መናገር የሚችሏቸውን ቋንቋዎች በመጥቀስ በጉባኤያቸው ውስጥ ላሉ መሪ የበላይ ተመልካቾች ሊያመለክቱ ይችላሉ። የጉባኤው የአገልግሎት ኮሚቴ እስከ ጥር 31, 1995 ድረስ እነዚህን ነጥቦች ከአስተያየታቸው ጋር በማከል ሊልኩልን ይገባል።

◼ በቅርቡ ይመጣሉ ተብለው የሚጠበቁ ጽሑፎች:-

ፈረንሳይኛ፦ አዲሲቱ ዓለም ትርጉም ፤ “ቅዱስ ጽሑፉ ሁሉ በአምላክ መንፈስ አነሣሺነት የተጻፈና ጠቃሚ ነው ”፤ ደስታን ማግኘት የሚቻልበት መንገድ፤ የአምላክ መንግሥት አዋጅ ነጋሪዎች የሆኑት የይሖዋ ምሥክሮች፤ “መንግሥትህ ትምጣ ”፤ ለዘላለም መኖር፤ ሕይወት እንዴት ተገኘ— በዝግመተ ለውጥ ወይስ በፍጥረት (ትንሹ)፤ የቤተሰብህን ኑሮ አስደሳች አድርገው፤ የሰው ልጅ አምላክን ለማግኘት ያደረገው ፍለጋ፤ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮችን መማሪያ መጽሐፌ፤ የወጣቶች ጥያቄ፤ የራእይ መደምደሚያው፤ ለይሖዋ የውዳሴ መዝሙር ዘምሩ (ትንሹ)፤ መጽሐፍ ቅዱስ የአምላክ ቃል ነው ወይስ የሰው?፤ እስከ ዛሬ ከኖሩት ሁሉ የሚበልጠው ታላቅ ሰው፤ እውነተኛ ሰላምና ደህንነት (አዲሱ)፤ አምላክ ስለ እኛ በእርግጥ ያስባልን?፤ በምድር ላይ ለዘላለም በደስታ ኑር!፤ ደም ሕይወትህን ሊያድን የሚችለው እንዴት ነው?፤ እንደ አንድ አካል ሆነው በዓለም ዙሪያ የአምላክን ፈቃድ የሚያደርጉት የይሖዋ ምሥክሮች፤ “እነሆ፣ ሁሉን አዲስ አደርጋለሁ”፤ በሥላሴ ማመን ይገባሃልን?፤ የሙታን መናፍስት ሊረዱህ ወይም ሊጎዱህ ይችላሉን? ለዘላለም ጸንቶ የሚኖረው መለኮታዊ ስም፤ የአምላክ መንግሥት ገነትን ታመጣለች፤ የሕይወት ዓላማ ምንድን ነው?

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ