የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 4/96 ገጽ 6
  • ቲኦክራሲያዊ ዜናዎች

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ቲኦክራሲያዊ ዜናዎች
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—1996
የመንግሥት አገልግሎታችን—1996
km 4/96 ገጽ 6

ቲኦክራሲያዊ ዜናዎች

አዲስ አበባ ውስጥ ስድስት አስፋፊዎች ያሉት አንድ ቤተሰብ ወርኃዊ የዘመቻ ጽሑፎችን በማበርከት በኩል ይሆናል የሚል መንፈስ በመያዝ ግሩም ምሳሌ ሆነዋል። እያንዳንዳቸው 10 መጻሕፍት ለማበርከት ግብ አወጡና በወሩ ውስጥ በአጠቃላይ 66 መጻሕፍት አበረከቱ።

በኢትዮጵያ የተደረጉት 17 ተከታታይ የልዩ ስብሰባ ፕሮግራሞች ተጠናቀዋል፤ በስብሰባው ላይ በጠቅላላው 8,694 ሰዎች የተገኙ ሲሆን 121 ሰዎች ተጠምቀዋል። ስብሰባው ለመጀመሪያ ጊዜ በተደረገባቸው በመቱና በመቀሌ ውስጥ 69 እና 119 ተሰብሳቢዎች ተገኝተዋል።

የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት በመምራት በኩል ልዩ አቅኚዎች ጥረት እያደረጉ ሲሆን ከእነዚህ መካከል ፊቼ፣ ክብረ መንግሥትና ናዝሬት የሚገኙ ልዩ አቅኚዎች እያንዳንዳቸው 15 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች አላቸው፣ አዲስ አበባ ውስጥ በቀበና ጉባኤ የሚገኙ 8 የዘወትር አቅኚዎች 31 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች አሏቸው (በተጨማሪም 31 መጽሐፎች አበርክተዋል)፣ አድዋ የሚገኙ 6 አስፋፊዎች 10 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች አላቸው፣ አዲግራት ውስጥ 5 አስፋፊዎች 6 ጥናቶች አላቸው፣ ዝዋይ 11 አስፋፊዎች 16 ጥናቶች ያላቸው ሲሆን ደብረ ታቦር 16 አስፋፊዎች 21 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች አላቸው።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ