ማስታወቂያዎች
◼ የሚበረከቱ ጽሑፎች:- የካቲት፦ ራእይ—ታላቁ መደምደሚያው ደርሷል! ወይም በጥር ወር ከሚበረከቱት መካከል ያላለቁት ጽሑፎች (ከ1984 በፊት የታተሙ ባለ 192 ገጽ መጻሕፍት)። መጋቢት፦ የቤተሰብ ደስታ የሚገኝበት ምሥጢር (እንግሊዝኛ) ወይም የቤተሰብህን ኑሮ አስደሳች አድርገው (አማርኛ)። ሚያዝያና ግንቦት፦ የመጠበቂያ ግንብ እና የንቁ! መጽሔት ነጠላ ቅጂዎች።
◼ ጸሐፊውና የአገልግሎት የበላይ ተመልካቹ የሁሉንም የዘወትር አቅኚዎች እንቅስቃሴ መመርመር ይኖርባቸዋል። የሰዓት ግባቸው ላይ ለመድረስ ያልቻሉ አቅኚዎች ካሉ እርዳታ የሚያገኙበትን መንገድ ሽማግሌዎቹ መቀየስ ይኖርባቸዋል። ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት በጥቅምት 1, 1993 (S-201) እና በጥቅምት 1, 1992 (S-201) የተላኩትን የማኅበሩን ደብዳቤዎች ተመልከቱ።
◼ በመጋቢት፣ በሚያዝያና በግንቦት ረዳት አቅኚ ሆነው ለማገልገል የሚፈልጉ አስፋፊዎች ሁኔታዎቻቸውን አሁኑኑ አስተካክለው ማመልከቻቸውን ቀደም ብለው ማስገባት ይኖርባቸዋል። እንዲህ ማድረጋቸው ሽማግሌዎች አስፈላጊ የሆኑ የመስክ አገልግሎት ዝግጅቶች እንዲያደርጉና በቂ መጠን ያላቸው መጽሔቶችና ጽሑፎች በጉባኤ ውስጥ መኖሩን እንዲያረጋግጡ ይረዳቸዋል። ረዳት አቅኚ ሆነው ለማገልገል ተቀባይነት ያገኙት ስማቸው ለጉባኤው መነበብ ይኖርበታል።
◼ በቅርቡ የደረሱን፦ ቱ ዚ ኤንድስ ኦቭ ዚ ኧርዝ፣ ዘ ኒው ወርልድ ሶሳይቲ ኢን አክሽን የተሰኙ የእንግሊዝኛ ቪድዮ ክሮች።