የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 2/98 ገጽ 3
  • “ይሖዋ ረዳቴ ነው”

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • “ይሖዋ ረዳቴ ነው”
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—1998
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • መንፈስ ቅዱስን የግል ረዳቴ አድርጌዋለሁን?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2000
  • ፍቅር ድፍረት ይጨምራል
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2006
  • ደፋሮች ሁኑ!
    መጠበቂያ ግንብ—1993
  • ‘ደፋሮችና ጠንካሮች ሁኑ!’
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2003
ለተጨማሪ መረጃ
የመንግሥት አገልግሎታችን—1998
km 2/98 ገጽ 3

“ይሖዋ ረዳቴ ነው”

1 ኢየሱስ የመጀመሪያዎቹን ደቀ መዛሙርቱን ለስብከት በላካቸው ጊዜ “እነሆ፣ እኔ እንደ በጎች በተኩላዎች መካከል እልካችኋለሁ” በማለት ነግሯቸው ነበር። (ማቴ. 10:16) ይህ የነገራቸው ነገር እንዲፈሩና መስበክ እንዲያቆሙ አድርጓቸዋልን? አላደረጋቸውም። ሐዋርያው ጳውሎስ ከጊዜ በኋላ ለእምነት ጓደኞቹ “በድፍረት:- ጌታ ይረዳኛልና አልፈራም ሰው ምን ያደርገኛል? እንላለን” በማለት የጻፈው ዓይነት አመለካከት ነበራቸው። (ዕብ. 13:6) ለኢየሱስ ስም ሲሉ ይናቁ ዘንድ የተገባቸው ሆነው ስለተቆጠሩ ተደስተዋል። እንዲሁም ያላንዳች ማሰለስ ምሥራቹን ማስተማራቸውንና ማወጃቸውን ቀጥለዋል።—ሥራ 5:41, 42

2 በዛሬው ጊዜ ዓለም አቀፉ የስብከት ሥራ የሚደመደምበት ደረጃ ላይ ደርሷል። ልክ ኢየሱስ እንደተነበየው በሁሉም ብሔራት ዘንድ የጥላቻ ዒላማ ሆነናል። (ማቴ. 24:9) የስብከት ሥራችን ተቃውሞና ትችት ደርሶበታል። እንዲያውም በአንዳንድ የምድር ክፍሎች ታግዷል። እምነት ባይኖረን ኖሮ ተስፋ መቁረጥ ይሰማን ነበር። ሆኖም ይሖዋ ረዳታችን እንደሆነ ማወቃችን ያነቃቃናል እንዲሁም ለመጽናት የሚያስችል ጥንካሬ ይሰጠናል።

3 ቆራጥነት የጥንካሬ፣ የድፍረትና የጀግንነት ባሕርይ መግለጫ ነው። ይህ ባሕርይ የፍርሃትና የወኔቢስነት ተቃራኒ ነው። የኢየሱስ ደቀ መዛሙርት ለመጽናት ዘወትር ቆራጥ መሆን አስፈልጓቸዋል። የአምላክ ጠላት የሆነው ዓለም በሚያሳየው ዝንባሌና በሚያደርገው ድርጊት በፍርሃት እንዳንዋጥ ይህ ባሕርይ አስፈላጊ ነው። ዓለምን ድል ያደረገው ኢየሱስ የተወውን የላቀ ምሳሌ መመልከት እንዴት የሚያበረታታ ነው! (ዮሐ. 16:33) ከዚህም በተጨማሪ ከባድ ፈተና ተደቅኖባቸው እያለ በድፍረት “ከሰው ይልቅ ለእግዚአብሔር ልንታዘዝ ይገባል” ያሉትን ሐዋርያት አስታውሱ።—ሥራ 5:29

4 ወደ ኋላ እንደሚያፈገፍጉት አይደለንም፦ ለሥራችን አዎንታዊ አመለካከት ለመያዝ ጥረት ማድረግ ይኖርብናል። (ዕብ. 10:39) ይሖዋ ይህን ተልዕኮ የሰጠን ለሰው ዘሮች ሁሉ ያለውን ፍቅርና ምሕረት ለመግለጽ እንደሆነ ዘወትር እናስታውስ። ምንም ጥቅም የሌለውን ነገር እንዲሠሩ አገልጋዮቹን በፍጹም አይጠይቅም። እንድንሠራው የተሰጠን ማንኛውም ዓይነት ሥራ ውሎ አድሮ አምላክን ለሚወዱ ሰዎች የሚጠቅም ነው።—ሮሜ 8:28

5 ይሆናል የሚል አመለካከት መያዛችን በክልላችን ውስጥ ያሉትን በግ መሰል ሰዎች መፈለጋችንን እንድንቀጥል ይረዳናል። ሰዎች የሚያሳዩት የግድየለሽነት ስሜት በውስጣቸው ያለውን ስጋትና ተስፋ መቁረጥ እንደሚገልጽ አድርገን ልንመለከተው እንችላለን። ለእነርሱ ያለን ፍቅር ሩሕሩሆችና ትዕግሥተኞች እንድንሆን ያድርገን። ጽሑፍ ባበረከትን ቁጥር ወይም ፍላጎት የማሳየት ጭላንጭል ካስተዋልን ሳንዘገይ ተመላልሶ መጠየቅ ለማድረግና ፍላጎቱን ይበልጥ ለማሳደግ ግብ ማድረግ ይኖርብናል። የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት የማስጀመር ወይም ውጤታማ በሆነ መንገድ የመምራት ችሎታችንን በፍጹም መጠራጠር የለብንም። ከዚህ ይልቅ ይሖዋ እንደሚረዳን በመተማመን ድጋፉንና አመራሩን እንዲሰጠን በጸሎት መጠየቅ ይኖርብናል።

6 ይሖዋ ሥራው እስኪጠናቀቅ ድረስ ድጋፍ መስጠቱን እንደሚቀጥል ጽኑ እምነት አለን። (ከፊልጵስዩስ 1:6 ጋር አወዳድር።) ይሖዋ ረዳታችን እንደመሆኑ መጠን በእርሱ ላይ ያለን ጽኑ እምነት ‘መልካም ሥራን ከመሥራት እንዳንታክት’ ያበረታናል።—ገላ. 6:9

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ