ማስታወቂያዎች
◼ የሚበረከቱ ጽሑፎች:- ሐምሌና ነሐሴ፦ ቀጥሎ ከተዘረዘሩት ባለ 32 ገጽ ብሮሹሮች መካከል ማንኛውንም ማበርከት ይቻላል:- በምድር ላይ ለዘላለም በደስታ ኑር!፣ በሥላሴ ማመን ይገባሃልን?፣ የአምላክ መንግሥት ገነትን ታመጣለች፣ የሙታን መናፍስት—ሊረዱህ ወይም ሊጎዱህ ይችላሉን? ደግሞስ በእርግጥ አሉን? እና ለዘላለም ጸንቶ የሚኖረው መለኮታዊው ስም። መስከረምና ጥቅምት፦ ለዘላለም መኖር።
◼ አምስት ቅዳሜና እሁዶች ያሉት የነሐሴ ወር በረዳት አቅኚነት ለማገልገል ለብዙዎች አመቺ ነው።
◼ ከመስከረም ወር አንስቶ የወረዳ የበላይ ተመልካቾች የሚሰጡት የሕዝብ ንግግር ጭብጥ “አካሄዳችሁን ከአምላክ ጋር አድርጋችኋልን?” የሚል ይሆናል።
◼ የጉባኤ ጸሐፊዎች ለፋይል የሚሆኑ ኮፒዎችን ለመሥራት በጉባኤ ሪፖርት መመለሻ ካርድ (S-1) መጠቀም እንደሌለባቸው ልናሳስባቸው እንወዳለን። እያንዳንዱ ጉባኤ የሚደርሰው የእነዚህ ካርዶች መጠን ለእያንዳንዱ ወር አንድ ነው። በS-1 ላይ የሰፈረውን የአገልግሎት እንቅስቃሴ ሪፖርት ኮፒ ለማስቀረት በሦስት የS-21 ካርዶች ላይ (አንድ ለዘወትር አቅኚዎች፣ አንድ ለረዳት አቅኚዎች፣ አንድ ለጉባኤ አስፋፊዎች) አኃዞቹን መገልበጡ የተሻለ ዘዴ ነው።
◼ በእንግሊዝኛ የሚካሄደውን የአውራጃ ስብሰባ ፕሮግራም ለማድረግ የታቀደው ከጥቅምት 23-25, 1998 ነው።