ቲኦክራሲያዊ ዜና
ጋና፦ በሚያዝያ 55,539 የደረሰ አዲስ ከፍተኛ የአስፋፊዎች ቁጥር ሪፖርት አድርጋለች። ይህም ካለፈው የአገልግሎት ዓመት አማካይ ቁጥር 9 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል። ከ200,000 የሚበልጡ ተሰብሳቢዎች በመታሰቢያው በዓል ላይ ተገኝተው ነበር።
ማላዊ፦ በአሁኑ ጊዜ የጉባኤዎች ቁጥር ከ600 በላይ ሆኗል። ይህም በጥቅምት 1967 እገዳ ሥር በነበሩበት ጊዜ ካለው የጉባኤዎች ቁጥር 50 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል።