የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 11/98 ገጽ 7
  • ማስታወቂያዎች

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ማስታወቂያዎች
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—1998
የመንግሥት አገልግሎታችን—1998
km 11/98 ገጽ 7

ማስታወቂያዎች

◼ የሚበረከቱ ጽሑፎች:- ኅዳርና-ታኅሣሥ፦ በምድር ላይ በገነት ለዘላለም መኖር ትችላለህ በ3:00 ብር። ጥር-የካቲት፦ መንግሥትህ ትምጣ፣ በሕይወት ተርፎ ወደ አዲስ ምድር መግባት ወይም እውነተኛው አንድ አምላክ ያስገኘው የአምልኮ አንድነት እያንዳንዳቸው በ3:00 ብር። እነዚህ መጻሕፍት የሌሏቸው ጉባኤዎች እነዚህን ጽሑፎች አሁን ማዘዝ ይኖርባቸዋል።

◼ ጉባኤዎች በኅዳር ወር በሚልኩት የጽሑፍ ማዘዣ ቅጽ ላይ የ1999 የይሖዋ ምሥክሮች የዓመት መጽሐፍ ማዘዝ መጀመር ይኖርባቸዋል። የዓመት መጽሐፍ በልዩ ትእዛዝ የሚገኝ መጽሐፍ ነው።

◼ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ወደ ውጪ አገር መሄድ የሚቻልበት አጋጣሚ ይበልጥ ክፍት እየሆነ መጥቷል። በመሆኑም ብዙ ወንድሞቻችንም ሌሎች አገሮችን የሚጎበኙበት ዝግጅት አድርገዋል። በተደጋጋሚ ከማኅበሩ ቅርንጫፍ ቢሮዎች መረጃ ይጠይቃሉ። ቅርንጫፍ ቢሮዎቹ በአካባቢያቸው ካሉት ጉባኤዎች ጋር እንዲገናኙ ለመርዳት የመንግሥት አዳራሽ አድራሻዎችንና ስብሰባ የሚደረግባቸውን ጊዜያት ለመጠቆም ዝግጁ ናቸው። እንዲሁም ቅርንጫፍ ቢሮውን መጎብኘትን በሚመለከት አስፈላጊ የሆኑ መመሪያዎችን ሊሰጧቸው ይችላሉ። ይሁን እንጂ የጉዞ ዝግጅቶችን፣ ማረፊያ ቦታዎችን፣ የሚጎበኙ ቦታዎችንና ሌሎች ከእነዚህ ጋር ተዛማጅነት ያላቸውን ጉዳዮች በሚመለከት ተጨማሪ ጥያቄዎች መቅረብ የሚኖርባቸው ለጎብኚዎች የመረጃ አገልግሎት ለሚሰጡት የጉዞ ወኪሎች ወይም አስጎብኚ ድርጅቶች መሆን ይኖርበታል።

◼ በቅርብ የደረሱን፦ አማርኛ፦ ስንሞት ምን እንሆናለን? (ብሮሹር)፣ ለቤተሰብ ደስታ ቁልፉ ምንድን ነው?፣ መጽሐፍ ቅዱስ—የአምላክ ቃል ነው ወይስ የሰው?፤ እንግሊዝኛ፦ ስለ አንተ የሚያስብ ፈጣሪ ይኖር ይሆን? (ለስላሳ ሽፋን) (ለአቅኚ 2.50፣ ለጉባኤ አስፋፊ 3.75)፣ ስንሞት ምን እንሆናለን?፣ የመጠበቂያ ግንብ ጽሑፎች ማውጫ 1997 የቴፕ ክሮች፦ ለቤተሰብ ደስታ ቁልፉ ምንድን ነው?፤ ትግርኛ፦ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች መማሪያ መጽሐፌ (ትንሹ እትም)፣ እስከ ዛሬ ከኖሩት ሁሉ የሚበልጠው ታላቅ ሰው (ለስላሳ ሽፋን)፣ ስንሞት ምን እንሆናለን? (ብሮሹር)፣ ለቤተሰብ ደስታ ቁልፉ ምንድን ነው?

◼ በድጋሚ ይመጣሉ ብለን የምንጠብቃቸው፦ እንግሊዝኛ፦ የቴፕ ክር፦ ይሖዋ የወሰዳቸው ፍርዶች።

የሚያስመሰግን ሥራ!

በነሐሴ የመንግሥት አገልግሎታችን ፊተኛ ገጽ ላይ የወጣው ርዕስ “በነሐሴ ልዩ የአገልግሎት እንቅስቃሴ ማድረግ ይቻል ይሆን?” የሚል ጥያቄ አቅርቦ ነበር። ይህ በሐምሌ የመንግሥት አገልግሎታችን ላይ “ወደ 6,000 ምን ያህል እንጠጋ ይሆን?” የሚለውን ጥያቄ ተከትሎ የቀረበ ጥያቄ ነበር። ሁሉም አዘውታሪ እንዲሆኑና አገልግሎታቸውን ሪፖርት በማድረጉ በኩል ንቁዎች እንዲሆኑ ልዩ ማበረታቻ ተሰጥቷል። በእርግጥም ለዚህ ማበረታቻ ተገቢውን ምላሽ ሰጥታችኋል! ዘግይተው የነበሩ የቆዩ ሪፖርቶችም ተመልሰዋል። በነሐሴ 6,021 የደረሰ አዲስ ከፍተኛ የአስፋፊዎች ቁጥር ላይ መድረሳችን ምንኛ ልብን በደስታ የሚያሞቅ ነው! ይህም ባለፈው የአገልግሎት ዓመት 6 በመቶ ጭማሪ እንዲገኝ አስተዋጽዖ አድርጓል ማለት ነው። በአገልግሎት አዘውታሪ መሆንንና ሪፖርታችንንም በጊዜው መመለስን ልማድ እናድርግ። በተጨማሪም ከመስከረም እስከ ታኅሣሥ ባሉት አራት ወራት ውስጥ እያንዳንዱ አስፋፊ ሦስት ቅጂዎችን እንዲያበረክት የወጣው ግብ ላይ ለመድረስ ሁላችሁም ጥረት ማድረጋችሁን ቀጥሉበት።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ