የመስከረም ወር የአገልግሎት ስብሰባዎች
መስከረም 6 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 84 (190)
10 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። ከመንግሥት አገልግሎታችን የተመረጡ ማስታወቂያዎች።
17 ደቂቃ፦ “የምትሠሩት በዓላማ ነውን?” አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ ክፍሉን በጥያቄና መልስ አቅርበው። አገልግሎታችን ከተባለው መጽሐፍ ከገጽ 88-9 ላይ ተጨማሪ ሐሳቦች አቅርብ። ሁሉም አገልግሎታቸውን ያለማሰለስና በተጣራ ሁኔታ እንዲያከናውኑ አበረታታ።
18 ደቂቃ፦ “ወላጆች—ለልጆቻችሁ ጥሩ ምሳሌ ሁኑ።” አንድ ሽማግሌ አጠር ያለ መግቢያ ካቀረበ በኋላ ልጆች ያሏቸው ሁለት ወንድሞች ርዕሱን በውይይት ያቀርቡታል። ልጆቻቸው በትምህርት ቤት፣ በቴሌቪዥንና የይሖዋ ምሥክር ባልሆኑ ዘመዶችና በሌሎች ሰዎች ላይ ለሚያዩት መጥፎ ባሕርያት የተጋለጡ በመሆናቸው እነርሱን ከአደጋ የመጠበቁ ጉዳይ እንዳሳሰባቸው ይገልጻሉ። ሁለቱ ወንድሞች አክብሮት ያለማሳየት ዝንባሌዎችን፣ ዓለማዊ አነጋገርንና አበጣጠርን እንዲሁም ጤናማ ያልሆነ መዝናኛን አንስተው ይወያያሉ። ጥሩ ምሳሌ መተው አስፈላጊ መሆኑን ከጠቀሱ በኋላ ለቤተሰብ ጥናት፣ ለጉባኤ ስብሰባዎችና ለመስክ አገልግሎት የበለጠ ግለት ማሳየት የሚቻልባቸውን መንገዶች ይወያያሉ።—የመስከረም 22, 1991 ንቁ! (እንግሊዝኛ) ገጽ 8-9ን ተመልከት።
መዝሙር 95 (213) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
መስከረም 13 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 81 (181)
10 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። የሒሳብ ሪፖርት።
15 ደቂቃ፦ ያለፈው ዓመት እንቅስቃሴያችን ምን ይመስል ነበር? በአገልግሎት የበላይ ተመልካቹ የሚቀርብ ንግግር። ከጉባኤው የ1999 የአገልግሎት ዓመት ሪፖርት ላይ ጎላ ያሉትን ነጥቦች ከልስ። ለተከናወኑት መልካም ሥራዎች ምስጋና አቅርብ። መሻሻል የሚያስፈልግባቸውን መስኮች ጥቀስ። ጉባኤው በተሰብሳቢዎች ቁጥርና በመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች ረገድ ያደረገው እንቅስቃሴ ምን ይመስል እንደነበር ትኩረት አድርግ። ለሁሉም ጉባኤዎች ከተላከው የሚያዝያ 2, 1999 ደብዳቤ ላይ ተስማሚ የሆኑ ነጥቦችን ጥቀስ። ለሚቀጥለው ዓመት ሊሠራባቸው የሚገባውን ተግባራዊ ግቦች ዘርዝር።
20 ደቂቃ፦ ጥሩ ምሳሌ የሚሆን ችሎታ ያለው አንድ ሽማግሌ “የአገልግሎት ክልላችንን ለመሸፈን ድፍረት ያስፈልጋል” የሚለውን ክፍል በጥያቄና መልስ ያቀርባል። እባክህ፣ አንቀጽ 5 እና 6ን አንብብ።
መዝሙር 20 (45) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
መስከረም 20 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 86 (193)
12 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎችና የመስክ አገልግሎት ተሞክሮዎች።
15 ደቂቃ፦ ከነሐሴ 1999 የመንግሥት አገልግሎታችን ላይ ከፊታችን ያለውን የአውራጃ ስብሰባ በሚመለከት ተስማሚ የሆኑ ነጥቦችን ከልስ።
18 ደቂቃ፦ በሚያዝያ 15, 1999 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 18-22 ላይ “ማንኛውንም መንፈሳዊ ድካም ማወቅና ማሸነፍ የሚቻልበት መንገድ” በሚለው ርዕስ ላይ የተመሠረተ ንግግር። ተግባራዊ የሆኑትን ነጥቦች በመከለስ ደምድም።
መዝሙር 78 (175) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
መስከረም 27 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 59 (139)
15 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። አስፋፊዎች የመስከረም ወር ሪፖርታቸውን እንዲመልሱ አሳስብ። በጥቅምት ወር ሁሉም መጽሔት በማሰራጨት የተሟላ ተሳትፎ ለማድረግ ዕቅድ እንዲያወጡ አበረታታ። በጥቅምት 1996 የመንግሥት አገልግሎታችን ገጽ 10 ላይ አቀራረቦችን እንዴት መዘጋጀት እንደሚቻል ከቀረቡት ሐሳቦች ውስጥ አንዳንዶቹን ከልስ። በቅርቡ የወጡትን መጽሔቶች በመጠቀም አንዳንድ ጥሩ የመነጋገሪያ ነጥቦችን ጥቀስና አንድ ወይም ሁለት አቀራረቦችን በሠርቶ ማሳያ አቅርብ።
15 ደቂቃ፦ የጥያቄ ሣጥን። በሽማግሌ የሚቀርብ ንግግር።
15 ደቂቃ፦ ለጉባኤው እንደሚያስፈልግ ተጠቀሙበት።
መዝሙር 40 (87) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
የአገልግሎት ስብሰባ . . . (ከገጽ 2 የዞረ)