የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 2/03 ገጽ 11
  • ማስታወቂያዎች

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ማስታወቂያዎች
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—2003
የመንግሥት አገልግሎታችን—2003
km 2/03 ገጽ 11

ማስታወቂያዎች

◼ የሚበረከቱ ጽሑፎች የካቲት:- ራእይ​—⁠ታላቁ መደምደሚያው ደርሷል! (በተመላልሶ መጠየቅ ወቅት ቢበረከት የተሻለ ይሆናል።) መጋቢት:- እውቀት መጽሐፍ የሚ​በረከት ሲሆን የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ለማስጀመር ጥረት ይደረጋል። ሚያዝያ እና ግንቦት:- መጠበቂያ ግንብ እና ንቁ! መጽሔቶች ይበረከታሉ። በመታሰቢያው በዓል ወይም በሌሎች ስብሰባዎች ላይ ለተገኙ ሆኖም ከጉባኤው ጋር አዘውትረው ለማይሰበሰቡ ሰዎችና ፍላጎት ላሳዩ ሌሎች ሰዎች ተመላልሶ መጠየቅ ስታደርጉ እውነተኛው አንድ አምላክ ያስገኘው የአምልኮ አንድነት የተባለውን መጽሐፍ ለማበርከት ጥረት አድርጉ። በተለይ እነዚህ ሰዎች እውቀት መጽሐፍን ወይም አምላክ ከእኛ የሚፈልገው የተባለውን ብሮሹር ከዚህ ቀደም አጥንተው ከነበረ የቤት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት በድጋሚ ለማስጀመር በተቻለ መጠን ጥረት አድርጉ።

◼ መጋቢት 1 ወይም ከዚያ ብዙም ሳይቆይ ሰብሳቢ የበላይ ተመልካቹ ወይም እርሱ የወከለው ሌላ ወንድም የጉባኤውን ሒሳብ መመርመር ይኖርበታል። የሚቀጥለው የሒሳብ ሪፖርት ከተነበበ በኋላ የሒሳብ ምርመራው ውጤት ለጉባኤው መነበብ አለበት። ጉባኤው ለዓለም አቀፉ ሥራና በድርጅቱ ለሚካሄዱ ሌሎች ሥራዎች ያደረገውን መዋጮ አስመልክቶ የተላከ የምስጋና ደብዳቤ ካለ ይነበብ።

◼ ጸሐፊውና የአገልግሎት የበላይ ተመልካቹ የሁሉንም የዘወትር አቅኚዎች የአገልግሎት እንቅስቃሴ መመርመር ይኖርባቸዋል። የሰዓት ግባቸው ላይ መድረስ ያልቻሉ አቅኚዎች ካሉ ሽማግሌዎቹ እርዳታ መስጠት የሚቻልበትን መንገድ መቀየስ ይኖርባቸዋል። ተጨማሪ ሐሳብ ለማግኘት የማኅበሩን ዓመታዊ S-201 ደብዳቤዎች ተመልከቱ። እንዲሁም የመስከረም 1986 የመንግሥት አገልግሎታችን አባሪ አንቀጽ 12-20ን ተመልከቱ።

◼ በመታሰቢያው በዓል ሰሞን የሚሰጠው የ2003 ልዩ የሕዝብ ንግግር ርዕስ “የባቢሎን የፍርድ ሰዓት ደርሷል?” የሚል ይሆናል። ከዚህ ጋር የተያያዙ ሌሎች ጉዳዮችን በሚመለከት በጥቅምት 2002 የመንግሥት አገልግሎታችን ላይ የወጣውን ማስታወቂያ ተመልከት።

◼ የግል የመጽሔት ኮንትራት ስለቀረ ጉባኤዎች የመጠበቂያ ግንብ እና የንቁ! መጽሔቶች እንደደረሷቸው ወዲያውኑ ለወንድሞች ማከፋፈል አለባቸው። ይህ አስፋፊዎች የግል ቅጂዎቻቸውን በወቅቱ እንዲያገኙና መጽሔቶቹን በመስክ አገልግሎት ላይ ከማበርከታቸው በፊት እንዲያነቡት ያስችላቸዋል።

◼ በ2003 ለሚደረጉት የአውራጃ ስብሰባዎች የወጣ ጊዜያዊ ፕሮግራም:-

መስ. 26-28አዲስ አበባእንግሊዝኛ

ጥቅ. 3-5አዲስ አበባአማርኛ/​የምልክት ቋንቋ

ጥቅ. 17-19ድሬዳዋአማርኛ

ጥቅ. 17-19ደሴአማርኛ

ጥቅ. 24-26ጅማአማርኛ

ጥቅ. 24-26መቀሌትግርኛ/​አማርኛ

ጥቅ. 31-ኅዳር 2ሻሸመኔአማርኛ

ጥቅ. 31-ኅዳር 2ነቀምትአማርኛ

ጥቅ. 31-ኅዳር 2ባሕር ዳርአማርኛ

ኅዳር 7-9ጊምቢኦሮምኛ

ኅዳር 7-9ሶዶአማርኛ

ኅዳር 7-9አለታ ወንዶአማርኛ

ኅዳር 14-16ሶዶወላይትኛ

ኅዳር 14-16አምቦኦሮምኛ

ኅዳር 14-16ይርጋለምሲዳምኛ

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ