የቲኦክራሲያዊ አገልግሎት ትምህርት ቤት ክለሳ
ሚያዝያ 26, 2010 በሚጀምር ሳምንት በቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ላይ መልስ የሚሰጥባቸው ጥያቄዎች የሚከተሉት ናቸው። የትምህርት ቤቱ የበላይ ተመልካች ከመጋቢት 1 እስከ ሚያዝያ 26, 2010 ድረስ ባሉት ሳምንታት ውስጥ በቀረቡት ክፍሎች ላይ የተመሠረተ የ20 ደቂቃ ክለሳ ይመራል።
1. ኑኃሚን ‘ይሖዋ አስጨነቀኝ፣ ሁሉን የሚችል አምላክ መከራ አመጣብኝ’ ስትል ምን ማለቷ ነበር? (ሩት 1:21) [w05 3/1 ገጽ 27 አን. 1]
2. ሩት “ምግባረ መልካም ሴት” እንድትባል ያደረጓት የትኞቹ ባሕርያት ናቸው? (ሩት 3:11) [w05 3/1 ገጽ 28 አን. 6]
3. ሕልቃና “ከዐሥር ወንዶች ልጆች እኔ አልበልጥብሽምን” ማለቱ ሚስቱን ያጽናናት እንዴት ነው? (1 ሳሙ. 1:8) [w90 3/15 ገጽ 27 አን. 5-6 (መግ 6-111 ገጽ 23 አን. 3-4)]
4. እስራኤላውያን ንጉሥ እንዲነግሥላቸው መጠየቃቸው ስህተት የነበረው ለምንድን ነው? (1 ሳሙ. 8:5) [w05 9/15 ገጽ 20 አን. 17፤ it-2 ገጽ 163 አን. 1]
5. ሳሙኤል ‘ዕድሜው ገፍቶና ጠጕሩ ሸብቶ’ በነበረበት ወቅት ለሌሎች በመጸለይ ረገድ ግሩም ምሳሌ የተወው እንዴት ነው? ይህስ የትኛውን ነጥብ ያጎላል? (1 ሳሙ. 12:2, 23) [w07 6/1 ገጽ 29 አን. 14-15]
6. ሳኦል ለቄናውያን ለየት ያለ ደግነት ያደረገላቸው ለምን ነበር? (1 ሳሙ. 15:6) [w05 3/15 ገጽ 22 አን. 10]
7. ሳኦል፣ “አንተ ወጣት፣ የማን ልጅ ነህ?” ብሎ ዳዊትን እንዲጠይቀው ያነሳሳው ምን ነበር? (1 ሳሙ. 17:58) [w07 8/1 ገጽ 31 አን. 3, 5]
8. ዳዊት በጌት ያጋጠመውን ከባድ ችግር ከተወጣበት መንገድ ምን ትምህርት እናገኛለን? (1 ሳሙ. 21:12, 13) [w05 3/15 ገጽ 24 አን. 4]
9. ዮናታን፣ ወዳጁ ዳዊት ማጽናኛና ማበረታቻ ባስፈለገው ወቅት ፍቅሩንና ትሕትናውን ያሳየው እንዴት ነው? (1 ሳሙ. 23:17) [lv ገጽ 28 አን. 10፣ የግርጌ ማስታወሻ]
10. ሳኦል በዓይንዶር ወደነበረችው ጠንቋይ ሄዶ ካጋጠመው ነገር ምን ትምህርት እናገኛለን? (1 ሳሙ. 28:8-19) [w05 3/15 ገጽ 24 አን. 7]