የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 3/11 ገጽ 6
  • ማስታወቂያዎች

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ማስታወቂያዎች
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—2011
የመንግሥት አገልግሎታችን—2011
km 3/11 ገጽ 6

ማስታወቂያዎች

◼ የሚበረከቱ ጽሑፎች፦ መጋቢት፦ ትክክለኛው የመጽሐፍ ስቅዱስ ትምህርት ምንድን ነው? ሚያዝያ እና ግንቦት፦ መጽሔቶች፤ ሰኔ፦ ትክክለኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ምንድን ነው?

◼ በሥራ ምክንያት ወደ ክልላችን የሚመጡ ቻይናውያን ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረበመሆኑ ከወትሮው የበለጠ ትኩረት ልንሰጣቸው እንፈልጋለን። በመሆኑም ትራክቶችንና አንዳንድ ጽሑፎችን እንድታዝዙ እናበረታታችኋለን። የሚከተሉት በቻይንኛ የተዘጋጁ ትራክቶች በእጃችን ይገኛሉ፦ T-23 (ይሖዋ)፣ T-26 (መጽሐፍ ቅዱስ)፣ T-27 (መከራና ሥቃይ ይወገዳል)፣ T-75 (መከራና ሥቃይ የሚያበቃበት ጊዜ ይኖር ይሆን? ለቡድሂስቶች)። የሚከተሉት ሦስት ብሮሹሮች ለቻይንኛ ቋንቋ ተናጋሪዎች የተዘጋጁ ናቸው፦ ኤ ሳቲስፋይንግ ላይፍ​—ሃው ቱ አቴይን ኢት (la)፣ ላስቲንግ ፒስ ኤንድ ሃፒነስ​—ሃው ቱ ፋይንድ ዘም (pc, ለቡድሂስቶች)፣ ዘ ፓዝዌይ ቱ ፒስ ኤንድ ሃፒነስ (ph, ለቡድሂስቶች)።

◼ የቻይንኛ ቋንቋ ተናጋሪ ለሆነ ሰው ስትመሠክሩ ማንበብ የሚፈልገው ቻይንኛ (Traditional Chinese) ነው ወይስ ቀለል ያለ ቻይንኛ (Chinese Simplified) የሚለውን ለማወቅ ለሰዎች ሁሉ ከተባለው ቡክሌት ላይ መልእክቱ በእነዚህ ቋንቋዎች የሚገኝባቸውን ገጾች አሳዩት። በጥቅሉ ሲታይ ከሆንግ ኮንግ ወይም ከታይዋን የመጡ ሰዎች በቻይንኛ (CH) የተዘጋጁ ጽሑፎችን ለማንበብ የሚመርጡ ሲሆን ከቻይና የሚመጡ ሰዎች ደግሞ ብዙ ጊዜ የሚመርጡት ቀለል ባለ ቻይንኛ (CHS) የተዘጋጁ ጽሑፎችን ነው። በኦዲዮ ወይም በቪዲዮ ከተዘጋጁት ጽሑፎች ጋር በተያያዘ ደግሞ የቤቱ ባለቤት አቀላጥፎ የሚናገረውና በደንብ የሚረዳው የትኛውን ቀበሌኛ እንደሆነ ለማወቅ ጥረት አድርጉ። በጥቅሉ ሲታይ ከቻይናና ከታይዋን የመጡ ሰዎች የማንደሪንን ቻይንኛ (CHM) የሚመርጡ ሲሆን ከሆንግ ኮንግ የመጡ ደግሞ የካንቶንን ቻይንኛ (CHC) ይመርጣሉ።

◼ የቻይንኛ ቋንቋ ተናጋሪ የሆኑ ሰዎችን በአካል አነጋግራችሁም ሆነ አድራሻቸውን አግኝታችሁ ከሆነ ለተመላልሶ መጠየቅ ዝግጅት እንዲደረግላቸው መረጃውን ወደ ቅርንጫፍ ቢሮ መላካችሁ የተገባ ነው። አድራሻውን ለመላክ እባካችሁ ተከታትላችሁ እርዱት (S-43) በሚለው ቅጽ መጠቀሙ የተሻለ ነው። አስፈላጊ ከሆነ የጉባኤው ጸሐፊ እንዲረዳችሁ መጠይቅ ትችላላችሁ።

◼ በነሐሴ ወር በአገልግሎት ስብሰባ ላይ ጂሆቫስ ዊትነስስ​—ኦርጋናይዝድ ቱ ሼር ዘ ጉድ ኒውስ (ምሥራቹን ለመስበክ የተደራጁት የይሖዋ ምሥክሮች) የተሰኘውን ፊልም እንከልሳለን። ፊልሙን ማግኘት የምትፈልጉ ከሆነ በተቻለ ፍጥነት በጉባኤው በኩል ማዘዝ ይኖርባችኋል።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ