የመስክ አገልግሎት ጎላ ያሉ ገጽታዎች
በኅዳርም ሆነ በታኅሣሥ ወር በ183 ጉባኤዎችና በ26 ቡድኖች ውስጥ የሚያገለግሉ ከ9,000 በላይ የሚሆኑ አስፋፊዎች ሪፖርት አድርገናል። በዚህ የአገልግሎት ዓመት በመጀመሪያዎቹ አራት ወራት ውስጥ 17 አዳዲስ ጉባኤዎች ተቋቁመዋል! መጽሐፍ ቅዱስ—የያዘው መልእክት ምንድን ነው? የተባለው ብሮሹር ዘመቻ በሚገባ ስለተከናወነ በኅዳር ወር 20,570 ብሮሹሮች ተበርክተዋል። በተጨማሪም በኅዳር ከ7,000 በላይ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች ሪፖርት መደረጋቸው በጣም አስደስቶናል። በየወሩ አዳዲስ ጥናቶችን ለማግኘትና ጥናት የጀመሩትን ዘወትር ለማስጠናት በትጋት መሥራታችሁን እንድትቀጥሉ እናበረታታችኋለን።