የመስክ አገልግሎት ጎላ ያሉ ገጽታዎች
በዚህ የአገልግሎት ዓመት በመጀመሪያዎቹ ስድስት ወራት ብቻ 3.2 በመቶ ጭማሪ ማግኘታችንን ስንገልጽላችሁ በጣም ደስ ይለናል። በልዩ ዘመቻው ሁለተኛው ወር ማለትም በየካቲት ወር 9,040 የደረሰ አዲስ ከፍተኛ የአስፋፊዎች ቁጥር አግኝተናል። እንዲሁም በዚህ ወር የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች ቁጥር 7,143 ነበር፤ ይህም ቢሆን አዲስ ከፍተኛ ቁጥር ነው። አሁን ያላችሁን ግሩም የሆነ የወንጌላዊነት መንፈስ ይዛችሁ እንድትቀጥሉ እናበረታታችኋለን!