የመስክ አገልግሎት ጎላ ያሉ ገጽታዎች
የግንቦት 2011 የኢትዮጵያ የመስክ አገልግሎት ሪፖርት በጣም የሚያበረታታ ነው። በዚያ ወር 9,192 አስፋፊዎች በአገልግሎት የተሳተፉ ሲሆን ይህም አዲስ ከፍተኛ ቁጥር ነው። ከእነዚህ መካከል 1,383 የሚያህሉት የዘወትር አቅኚዎች ናቸው። ከመጪው መስከረም ጀምሮ ብዙዎች ወደዚህ የአገልግሎት ዘርፍ እንደሚገቡ ተስፋ እናደርጋለን። ዘወትር አቅኚ ለመሆን የምታስቡ ከሆነ የማመልከቻ ቅጹን ሞልታችሁ ሳትዘገዩ ለጉባኤያችሁ የአገልግሎት ኮሚቴ እንድትሰጡ እናበረታታችኋለን፤ ይህም ኮሚቴው ቅጹን ቶሎ ወደ ቅርንጫፍ ቢሮው እንዲልክ ያስችለዋል። በተጨማሪም በግንቦት ወር 7,311 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች ተመርተዋል፤ ይህም ሲባል እያንዳንዱ አስፋፊ በአማካይ 0.3 ጥናት አለው ማለት ነው። አንተስ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት አለህ? በአገልግሎት ላይ ለምታደርጉት ቅንዓት የተሞላበት ተሳትፎ ልናመሰግናችሁ እንወዳለን።