የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 10/12 ገጽ 8
  • የመስክ አገልግሎት ጎላ ያሉ ገጽታዎች

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የመስክ አገልግሎት ጎላ ያሉ ገጽታዎች
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—2012
የመንግሥት አገልግሎታችን—2012
km 10/12 ገጽ 8

የመስክ አገልግሎት ጎላ ያሉ ገጽታዎች

ፍላጎት ያላቸውን ሰዎች ለክርስቶስ ሞት መታሰቢያ ለመጋበዝ ያደረግነው ጥረት በጣም አስደሳች ውጤት አስገኝቷል። በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ 194 ጉባኤዎች ያሉ ቢሆንም ሪፖርት የተደረገው ግን ከ219 ቦታዎች ነው። ከእነዚህ መካከል በስድስቱ የመታሰቢያ በዓሉ የተከበረው ለመጀመሪያ ጊዜ ነው። በበዓሉ ላይ የተገኙት ሰዎች አጠቃላይ ቁጥር 23,762 ሲሆን ይህ ደግሞ ተከታትለን ልንረዳቸው የሚገባ ብዙ ሰዎች እንዳሉ ይጠቁማል። በበርካታ ቦታዎች የተሰብሳቢዎቹ ቁጥር ከአስፋፊዎቹ ቁጥር በብዙ እጥፍ ይበልጥ ነበር። ከእነዚህ መካከል ጥቂቶቹ የሚከተሉት ናቸው፦ አለታ ወንዶ፦ 233 (54 አስፋፊዎች)፣ አረካ፦ 124 (15 አስፋፊዎች)፣ ቦንጋ፦ 80 (19 አስፋፊዎች)፣ ገደብ፦ 170 (33 አስፋፊዎች)፣ ገልሞ ወረቦ ወሊሶ አካባቢ፦ 138 (15 አስፋፊዎች)፣ ሂርና፦ 57 (5 አስፋፊዎች)፣ ሆሳዕና፦ 104 (24 አስፋፊዎች)፣ ሲባጫሮ ጊምቢ አካባቢ 364 (71 አስፋፊዎች) እና ይርጋጨፌ 118 (13 አስፋፊዎች)።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ