የቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ክለሳ
ታኅሣሥ 31, 2012 በሚጀምር ሳምንት በቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ላይ መልስ የሚሰጥባቸው ጥያቄዎች የሚከተሉት ናቸው። እያንዳንዱ ነጥብ ውይይት የሚደረግበት መቼ እንደሆነ የሚጠቁም ቀን በጥያቄዎቹ ላይ የተካተተው በየሳምንቱ ለትምህርት ቤቱ ዝግጅት በምናደርግበት ወቅት ምርምር እንድናደርግ ታስቦ ነው።
1. በኢዩኤል 2:1-10, 28 ላይ የሚገኘው ምድሪቱ በነፍሳት ሠራዊት ስለ መወረሯ የተነገረው ትንቢት ፍጻሜውን ያገኘው እንዴት ነው? [ኅዳር 5, w07 10/1 ገጽ 13 አን. 1]
2. አሞጽ 8:11 ፍጻሜውን ያገኘው በማን ላይ ነው? መንፈሳዊ ምግብ በተትረፈረፈበት ጊዜ እንደመኖራችን መጠን ራሳችንን ምን ብለን መጠየቅ ይኖርብናል? [ኅዳር 12, jd-E ገጽ 60-61 አን. 9]
3. ኤዶማውያን ልባቸው በትዕቢት እንዲወጠር ያደረገው ምን ሊሆን ይችላል? እኛስ የትኛውን እውነታ መዘንጋት አይኖርብንም? (አብ. 3, 4) [ኅዳር 19, w07 11/1 ገጽ 14 አን. 1]
4. ይሖዋ በነነዌ ነዋሪዎች ላይ እንደሚያመጣ ከተናገረው መዓት ጋር በተያያዘ ተጸጽቷል ሊባል የሚችለው እንዴት ነው? (ዮናስ 3:8, 10 የ1954 ትርጉም) [ኅዳር 19, w07 11/1 ገጽ 15 አን. 1]
5. በአምላክ ስም መሄድ ሲባል ምን ማለት ነው? ይህን ማድረጋችንስ ከእሱ ጋር ያለንን ወዳጅነት የሚያጠናክረው እንዴት ነው? (ሚክ. 4:5) [ኅዳር 26, uw ምዕ. 2 አን. 13-14 ፤ jd-E ገጽ 88 አን. 12]
6. በናሆም 2:6-10 ላይ ያለው ትንቢት መፈጸሙ ስለ ምን ነገር እርግጠኛ እንድንሆን ያደርገናል? [ታኅ. 3, w07 11/15 ገጽ 9 አን. 2፤ w88-E 2/15 ገጽ 28 አን. 7]
7. የሐጌ 1:6 ትርጉም ምንድን ነው? ከዚህስ ምን ጠቃሚ ትምህርት እናገኛለን? [ታኅ. 10, w06 4/15 ገጽ 22 አን. 12-15]
8. በዘካርያስ 7:10 ላይ የሚገኘውን በልባችን ‘አንዳችን በሌላው ላይ ክፉ እንዳናስብ’ የተሰጠንን ምክር ተግባራዊ ማድረግ የምንችለው እንዴት ነው? [ታኅ. 17, jd-E ገጽ 113 አን. 6፤ w07 12/1 ገጽ 11 አን. 2]
9. በዘካርያስ 4:6, 7 ላይ የሚገኙት ቃላት በዛሬው ጊዜ ያሉ የይሖዋ አገልጋዮችን የሚያጽናኑት እንዴት ነው? [ታኅ. 17, w07 12/1 ገጽ 10 አን. 7]
10. በሚልክያስ 3:16 ላይ ከሰፈረው ዘገባ አንጻር ለአምላክ ያለንን ታማኝነት ጠብቀን ለመመላለስ የያዝነውን ቁርጥ አቋም ፈጽሞ ማላላት የማይኖርብን ለምንድን ነው? [ታኅ. 31, w07 12/15 ገጽ 29 አን. 3]