ማስታወቂያዎች
◼ የሚበረከቱ ጽሑፎች፦ ጥር እና የካቲት፦ ከሚከተሉት ባለ32 ገጽ ብሮሹሮች አንዱን ማበርከት ትችላላችሁ፦ አምላክ ስለ እኛ በእርግጥ ያስባልን?፣ የምትወዱት ሰው ሲሞት ወይም የአምላክ ወዳጅ መሆን ትችላለህ! ተመላልሶ መጠየቅ ስታደርጉ የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት የተባለውን መጽሐፍ አሊያም ደግሞ የግለሰቡን ሁኔታ ግምት ውስጥ በማስገባት አምላክን ስማ ወይም አምላክን ስማ የዘላለም ሕይወት ታገኛለህ ከተባሉት ብሮሹሮች መካከል አንዱን በማበርከት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ለማስጀመር ጥረት አድርጉ። መጋቢት እና ሚያዝያ፦ መጠበቂያ ግንብ እና ንቁ! መጽሔቶች። ተመላልሶ መጠየቅ ስታደርጉ የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት የተባለውን መጽሐፍ አሊያም ደግሞ የግለሰቡን ሁኔታ ግምት ውስጥ በማስገባት አምላክን ስማ ወይም አምላክን ስማ የዘላለም ሕይወት ታገኛለህ ከተባሉት ብሮሹሮች መካከል አንዱን በማበርከት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ለማስጀመር ጥረት አድርጉ።
◼ በ2013 የአገልግሎት ዓመት ሁለተኛ አጋማሽ ላይ የወረዳ የበላይ ተመልካቾች የሚሰጡት የሕዝብ ንግግር ‘ለሁሉም ብሔራት፣ ነገዶችና ቋንቋዎች የሚሆን ምሥራች’ የሚል ጭብጥ ይኖረዋል።
◼ የሚከተሉት አዳዲስ ጽሑፎች ስለደረሱን ማዘዝ ትችላላችሁ፦ አማርኛ፦ “ተከታዬ ሁን”፤ ኦሮምኛ፦ ወደ ይሖዋ ቅረብ፤ ትግርኛ፦ የግሪክኛ ቅዱሳን መጻሕፍት አዲስ ዓለም ትርጉም፤ ወላይትኛ፦ የቤተሰብ ደስታ፣ የሕይወት ዓላማ።