ማስታወቂያዎች
መጋቢት እና ሚያዝያ፦ መጠበቂያ ግንብ እና ንቁ! መጽሔቶች። ግንቦት እና ሰኔ፦ ትራክቶች።
የመታሰቢያው በዓል የሚከበረው ሰኞ፣ ሚያዝያ 14 ቀን 2014 ነው። ጉባኤያችሁ ሰኞ ዕለት ስብሰባ የሚያደርግ ከሆነ በዚያ ሳምንት የመንግሥት አዳራሹ ነፃ ወደሚሆንበት ሌላ ቀን ማዛወር ይኖርባችኋል። የአገልግሎት ስብሰባውን መሰረዝ ግድ ከሆነ ግን በዚያ ሳምንት ላይ ከሚቀርቡት ክፍሎች መካከል ለጉባኤያችሁ አስፈላጊ የሆኑትን በዚያው ወር ውስጥ በሌላ ጊዜ እንዲቀርቡ ለማድረግ የሽማግሌዎች አካል አስተባባሪው በፕሮግራሙ ላይ ማስተካከያ ማድረግ ይችላል።