የመስክ አገልግሎት ጎላ ያሉ ገጽታዎች
መጋቢት ልዩ የአገልግሎት እንቅስቃሴ የተደረገበት ወር ነበር፤ በመሆኑም በአስፋፊዎች፣ በተበረከቱ መጽሔቶችና በመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች ብዛት ረገድ አዲስ ከፍተኛ ቁጥር አግኝተናል! በዚህ ወር በተካሄደው ልዩ ዘመቻም ቢሆን በርካታ ግሩም ተሞክሮዎች ተገኝተዋል፤ ሰዎች በመታሰቢያው በዓል ላይ እንዲገኙ መጋበዝ የጀመርነውም ቢሆን በዚህ ወር ነው። ብዙዎች ረዳት አቅኚ ሆነው አገልግለዋል። ሪፖርት ከተደረጉት 9,837 አስፋፊዎች መካከል ግማሽ ገደማ ማለትም 44 በመቶ የሚሆኑት በአንድ ዓይነት የአቅኚነት አገልግሎት ተካፍለዋል። በእርግጥም ይበል የሚያሰኝ ነው!