ማስታወቂያዎች
◼ መጋቢት እና ሚያዝያ፦ መጠበቂያ ግንብ እና ንቁ! መጽሔቶች። ግንቦት እና ሰኔ፦ ትክክለኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ምንድን ነው? ወይም ከሚከተሉት ትራክቶች አንዱን ማበርከት ትችላላችሁ፦ ስለ መጽሐፍ ቅዱስ ምን አመለካከት አለህ? (T-30)፣ ስለ ወደፊቱ ጊዜ ምን ይሰማሃል? (T-31)፣ የቤተሰብን ሕይወት አስደሳች ለማድረግ ቁልፉ ምንድን ነው? (T-32)፣ ዓለምን እየተቆጣጠረ ያለው ማን ነው? (T-33)፣ መከራ የማይኖርበት ጊዜ ይመጣል? (T-34)፣ የሞቱ ሰዎች እንደገና በሕይወት መኖር ይችላሉ? (T-35)፣ የአምላክ መንግሥት ምንድን ነው? (T-36)፣ በአእምሯችን ለሚጉላሉ ጥያቄዎች መልስ ማግኘት የሚቻለው ከየት ነው? (T-37) እና እውነቱን ማወቅ ትፈልጋለህ? (kt)።
◼ የመታሰቢያው በዓል የሚከበረው ዓርብ፣ መጋቢት 25 ቀን 2007 ዓ.ም. (ሚያዝያ 3 ቀን 2015) ነው። ጉባኤያችሁ ዓርብ ዕለት ስብሰባ የሚያደርግ ከሆነ በዚያ ሳምንት የመንግሥት አዳራሹ ነፃ ወደሚሆንበት ሌላ ቀን ማዛወር ይኖርባችኋል። የአገልግሎት ስብሰባውን መሰረዝ ግድ ከሆነ ግን በዚያ ሳምንት ላይ ከሚቀርቡት ክፍሎች መካከል ለጉባኤያችሁ አስፈላጊ የሆኑትን በዚያው ወር ውስጥ በሌላ ጊዜ እንዲቀርቡ ለማድረግ የሽማግሌዎች አካል አስተባባሪው በፕሮግራሙ ላይ ማስተካከያ ማድረግ ይችላል።