የመስክ አገልግሎት ጎላ ያሉ ገጽታዎች
ባለፈው የአገልግሎት ዓመት በአስፋፊዎች ብዛት ረገድ 3 በመቶ ጭማሪ አግኝተናል። የተጠማቂዎች ብዛት 513 ሲሆን 22 ግለሰቦች ማንበብና መጻፍ ተምረዋል። አዳዲሶቹን ተጠማቂዎች በደስታ ልንቀበላቸው እንወዳለን፤ እንዲሁም ተጨማሪ ሰዎች መንፈሳዊ ምግብ የያዙትን ጽሑፎች ማንበብ በመማራቸው ተደስተናል። አስተማሪዎቻቸው ላከናወኑት ሥራ ሊመሰገኑ ይገባል፤ ሁላችሁም ብትሆኑ ማንበብና መጻፍ የማይችሉ ሰዎችን ለመርዳት በምታደርጉት ጥረት እንድትገፉ እናበረታታችኋለን። ባለፈው ዓመት የተበረከቱት መጽሔቶች ብዛት 23 በመቶ፣ መጻሕፍት 38 በመቶ፣ ብሮሹሮች ደግሞ (ትራክቶችን ይጨምራል) 845 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል። ይህም በርካታ ሰዎች በአምላክ ቃል ውስጥ የሚገኘውን ውድ እውነት የማወቅ አጋጣሚ እንዲያገኙ ስለሚያደርግ በጣም የሚያስደስት ነው። ሁላችንም ጽሑፎቻችንን በተለይም መጽሔቶችንና ትራክቶችን ውጤታማ በሆነ መንገድ መጠቀማችንን እንቀጥል። በሌላ በኩል ደግሞ ፍላጎት ያሳዩ ሰዎችን መዝግቦ በመያዝና ተመላልሶ መጠየቅ በማድረግ የተዘራውን ውድ የሆነ ዘር ‘እንድታጠጡ’ እናበረታታችኋለን።—1 ቆሮ. 3:6