ማስታወቂያዎች
◼ የሚበረከቱ ጽሑፎች፦ መስከረም እና ጥቅምት፦ መጠበቂያ ግንብ እና ንቁ! መጽሔቶች። ኅዳር እና ታኅሣሥ፦ ትክክለኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ምንድን ነው? ወይም ከሚከተሉት ትራክቶች አንዱን ማበርከት ትችላላችሁ፦ ስለ መጽሐፍ ቅዱስ ምን አመለካከት አለህ? (T-30)፣ ስለ ወደፊቱ ጊዜ ምን ይሰማሃል? (T-31)፣ የቤተሰብን ሕይወት አስደሳች ለማድረግ ቁልፉ ምንድን ነው? (T-32)፣ ዓለምን እየተቆጣጠረ ያለው ማን ነው? (T-33)፣ መከራ የማይኖርበት ጊዜ ይመጣል? (T-34)፣ የሞቱ ሰዎች እንደገና በሕይወት መኖር ይችላሉ? (T-35)፣ የአምላክ መንግሥት ምንድን ነው? (T-36)።
◼ በ2016 በሚከበረው የመታሰቢያው በዓል ሰሞን የሚሰጠው ልዩ የሕዝብ ንግግር መጋቢት 28 በሚጀምረው ሳምንት ይቀርባል። የንግግሩ ርዕስ ወደፊት ይገለጻል። በዚያ ሳምንት የወረዳ ስብሰባ ወይም የወረዳ የበላይ ተመልካች ጉብኝት ያላቸው ጉባኤዎች ልዩ የሕዝብ ንግግሩን በቀጣዩ ሳምንት ማቅረብ ይችላሉ። በየትኛውም ጉባኤ ልዩ የሕዝብ ንግግሩ ከመጋቢት 28 በፊት መቅረብ አይኖርበትም።