የመስክ አገልግሎት ጎላ ያሉ ገጽታዎች
በዚህ ዓመት የመታሰቢያውን በዓል የመጋበዣ ወረቀት የማሰራጨት ዘመቻ የተጀመረው ቅዳሜ፣ መጋቢት 7, 2015 ነበር። በሦስት የአገልግሎት ዘርፎች አዲስ ከፍተኛ ቁጥር መመዝገቡን ስናሳውቃችሁ ደስ ይለናል፤ የተበረከቱ ቡክሌቶች ቁጥር፦ 415,417፤ መጽሔቶች፦ 126,189፤ ተመላልሶ መጠየቅ፦ 133,635። በተጨማሪም በመጋቢት 2015፣ 2,123 አስፋፊዎች አገልግሎታቸውን በማስፋት ረዳት አቅኚ ሆነው እንዳገለገሉ ስናሳውቃችሁ በጣም ደስ ይለናል። ከላይ በተጠቀሱት ሦስት የአገልግሎት ዘርፎች የተመዘገበው አዲስ ከፍተኛ ቁጥር እንደሚያሳየው በዚያ ወር የተከናወነው ልዩ የአገልግሎት እንቅስቃሴ በእርግጥም በጣም አስደሳች ነው!—መዝ. 110:3