የመስክ አገልግሎት ጎላ ያሉ ገጽታዎች
በዚህ ዓመት ኢትዮጵያ ውስጥ አራት ጉባኤዎችና ገለልተኛ በሆኑ አካባቢዎች የሚገኙ ስምንት ቡድኖች መቋቋማቸውን ስናሳውቃችሁ ደስ ይለናል። በአሁኑ ጊዜ በአገሪቱ በጠቅላላ 217 ጉባኤዎች ያሉ ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ 70ዎቹ የሚገኙት በአዲስ አበባ ነው። የስብከቱን ሥራ ለማስፋፋት የምናከናውነው ገና ብዙ ሥራ አለ። ይሖዋ እሱን ለማክበር ኃይላቸውን የሚጠቀሙ ሁሉ በትጋት የሚያከናውኑትን ሥራ እንደሚባርክ እንተማመናለን።
በተጨማሪም ዓይነ ስውራንን ለመርዳት ሲባል የብሬይል ጽሑፎች በአማርኛ ለመጀመሪያ ጊዜ መውጣታቸውን ስንገልጽላችሁ ደስ ይለናል። ይህ ዝግጅት በኢሳይያስ 35:5 ላይ የሚገኘውን ትንቢት ፍጻሜ የሚጠባበቁ ሁሉ መንፈሳዊ ዓይናቸው እንዲበራ ይረዳቸዋል ብለን ተስፋ እናደርጋለን።