የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • mwb17 መጋቢት ገጽ 7
  • እስራኤል ይሖዋን ረስቷል

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • እስራኤል ይሖዋን ረስቷል
  • ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2017
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ይሖዋ ኤርምያስን እንዲሰብክ ላከው
    ከመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች ምን ትማራለህ?
  • የኤርምያስ መጽሐፍ ጎላ ያሉ ነጥቦች
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2007
  • ኤርምያስ ስለ ይሖዋ መናገሩን አላቆመም
    ልጆቻችሁን አስተምሩ
  • እንደ ኤርምያስ ደፋር ሁኑ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2004
ለተጨማሪ መረጃ
ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2017
mwb17 መጋቢት ገጽ 7

ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት | ኤርምያስ 12–16

እስራኤል ይሖዋን ረስቷል

ይሖዋ የይሁዳን ኩራትና የኢየሩሳሌምን እብሪት ለማጥፋት ውሳኔ አድርጎ ነበር፤ ኤርምያስ ይህን ጥፋት በምሳሌ ማሳየትን የሚጠይቅ ተፈታታኝ ተልእኮ ተሰጥቶት ነበር

ኤርምያስ ከኢየሩሳሌም ወደ ኤፍራጥስ ወንዝ ሁለት ጊዜ የደርሶ መልስ ጉዞ አድርጓል

ኤርምያስ ከተልባ እግር የተሠራ ቀበቶ ገዛ

13:1, 2

  • ቀበቶ በሰው ወገብ ላይ እንደሚጣበቅ ሁሉ የእስራኤል ብሔርም በምሳሌያዊ ሁኔታ ከይሖዋ ጋር መጣበቅ ይችል ነበር

ኤርምያስ ቀበቶውን ይዞ ወደ ኤፍራጥስ ወንዝ ሄደ

13:3-5

  • ቀበቶውን በቋጥኝ ስንጥቅ ውስጥ ከደበቀው በኋላ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሰ

ኤርምያስ ቀበቶውን ለማምጣት ወደ ኤፍራጥስ ወንዝ ተመልሶ ሄደ

13:6, 7

  • ቀበቶው ተበላሽቶ አገኘው

ኤርምያስ ተልእኮውን ከተወጣ በኋላ ይሖዋ ስለ ጉዳዩ አብራራለት

13:8-11

  • ኤርምያስ ያደረገው ነገር ምንም ጥቅም የሌለው ሊመስል ቢችልም በፈቃደኝነት ታዟል፤ እንዲህ ማድረጉ ይሖዋ የሕዝቡን ልብ ለመንካት ባደረገው ጥረት ትልቅ አስተዋጽኦ እንዲያበረክት አስችሎታል

ይህን ታውቅ ነበር?

ከኢየሩሳሌም እስከ ኤፍራጥስ ወንዝ ድረስ ያለው ርቀት 500 ኪ.ሜ. (300 ማይል) ገደማ ይሆናል። ኤርምያስ ወደዚህ ቦታ ሁለት ጊዜ ደርሶ ለመመለስ ወደ 2,000 ኪ.ሜ. (1,200 ማይል) ገደማ መጓዝ ነበረበት፤ ይህ ምናልባትም ለወራት መጓዝን ይጠይቃል።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ