የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • mwb17 ጥቅምት ገጽ 3
  • ትጉ የመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪ መሆን የሚቻለው እንዴት ነው?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ትጉ የመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪ መሆን የሚቻለው እንዴት ነው?
  • ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2017
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ይሖዋ ለዳንኤል ቃል የገባለት አስደናቂ በረከት
    የዳንኤልን ትንቢት በትኩረት ተከታተል!
  • አምላክ በእርግጥ ስለ አንተ ያስባል?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2011
  • የዳንኤል መጽሐፍና አንተ
    የዳንኤልን ትንቢት በትኩረት ተከታተል!
  • በፍጻሜው ዘመን ያሉትን እውነተኛ አምላኪዎች ለይቶ ማወቅ
    የዳንኤልን ትንቢት በትኩረት ተከታተል!
ለተጨማሪ መረጃ
ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2017
mwb17 ጥቅምት ገጽ 3

ክርስቲያናዊ ሕይወት

ትጉ የመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪ መሆን የሚቻለው እንዴት ነው?

ፈተናዎች ሲደርሱብህ ልክ እንደ ዳንኤል ፈተናዎቹን በታማኝነት መወጣት ትፈልጋለህ? ዳንኤል ጥልቅ የሆኑ ትንቢቶችን ጨምሮ የአምላክን ቃል በትጋት ያጠና ነበር። (ዳን 9:2) መጽሐፍ ቅዱስን በትጋት ማጥናትህ ምንጊዜም ታማኝ እንድትሆን ይረዳሃል። እንዴት? ይሖዋ ቃል የገባቸው ነገሮች እንደሚፈጸሙ ያለህን እምነት ያጠናክርልሃል። (ኢያሱ 23:14) በተጨማሪም ለይሖዋ ያለህን ፍቅር ለማሳደግ ይረዳሃል፤ ይህም ትክክል የሆነውን ነገር እንድታደርግ ያነሳሳሃል። (መዝ 97:10) ይሁንና መጽሐፍ ቅዱስን በትጋት የማጥናት ልማድ ለማዳበር ከየት መጀመር ትችላለህ? እስቲ የሚከተሉትን ጠቃሚ ሐሳቦች ተመልከት።

ዳንኤል የአምላክን ቃል ሲያጠና
  • ምን ማጥናት እችላለሁ? ጥሩ የጥናት ልማድ፣ ለጉባኤ ስብሰባዎች መዘጋጀትን ይጨምራል። ሳምንታዊውን የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ስታነብ ግልጽ ባልሆኑልህ ነጥቦች ላይ ምርምር ለማድረግ ጊዜ የምትመድብ ከሆነ ከንባቡ ይበልጥ ጥቅም ማግኘት ትችላለህ። በተጨማሪም ስለ መጽሐፍ ቅዱስ ትንቢቶች፣ ስለ አምላክ መንፈስ ፍሬ የተለያዩ ገጽታዎች፣ ሐዋርያው ጳውሎስ ስላደረጋቸው ሚስዮናዊ ጉዞዎች ሌላው ቀርቶ ይሖዋ ስለፈጠራቸው ግዑዛን ፍጥረታት ይበልጥ ለማወቅ ምርምር ማድረግ ይቻላል። ከዚህም ሌላ በቀኑ ውስጥ አንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄ ወደ አእምሮህ ከመጣ ጥያቄውን በማስታወሻ ላይ በመጻፍ በቀጣዩ የጥናት ፕሮግራምህ ላይ ምርምር ልታደርግበት ትችላለህ።

  • ምርምር ለማድረግ የትኞቹን መሣሪያዎች መጠቀም እችላለሁ? አንዳንድ አማራጮችን ለማግኘት መንፈሳዊ ዕንቁዎችን ለማግኘት የሚረዱ የምርምር መሣሪያዎች የሚለውን ቪዲዮ ተመልከት። ለልምምድ ያህል፣ በዳንኤል ምዕራፍ 7 ላይ የተጠቀሱት አውሬዎች የትኞቹን የዓለም ኃይሎች እንደሚወክሉ በምርምር ለማግኘት ሞክር።

  • ለጥናት ምን ያህል ጊዜ መመደብ ይኖርብኛል? ቋሚ የጥናት ፕሮግራም በመንፈሳዊ ጤናማ ለመሆን ወሳኝ ነገር ነው። አጠር አጠር ባሉ የጥናት ፕሮግራሞች መጀመርና በጥናት የምታሳልፈውን ጊዜ ቀስ በቀስ እየጨመርክ መሄድ ትችላለህ። የአምላክን ቃል ማጥናት የተሸሸጉ ሀብቶችን ለማግኘት ከመቆፈር ጋር ሊመሳሰል ይችላል፤ የተሸሸጉ ሀብቶችን ባገኘህ ቁጥር ይበልጥ ለመቆፈር ትነሳሳለህ! (ምሳሌ 2:3-6) በተመሳሳይም በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያሉትን የተሸሸጉ ሀብቶች ባገኘህ ቁጥር ለአምላክ ቃል ያለህ ጉጉት እየጨመረ ስለሚሄድ መጽሐፍ ቅዱስን ማጥናት ቋሚ የሕይወትህ ክፍል ይሆናል።—1ጴጥ 2:2

    የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናትህን አስደሳች ማድረግ የምትችልበትን መንገድ በተመለከተ ጠቃሚ ምክሮችን ለማግኘት የካቲት 2012 ንቁ! ገጽ 18-20⁠ን ተመልከት።

በዳንኤል ምዕራፍ 7 ላይ የተጠቀሱት አውሬዎች እነማንን ይወክላሉ?

  • የንሥር ክንፎች ያሉት አንበሳ የሚመስል አውሬ

    ዳን 7:4

  • በአፉ ሦስት የጎድን አጥንቶች የያዘ ድብ የሚመስል አውሬ

    ዳን 7:5

  • አራት ራሶችና አራት ክንፎች ያሉት ነብር የሚመስል አውሬ

    ዳን 7:6

  • ትላልቅ የብረት ጥርሶችና አሥር ቀንዶች ያሉት አስፈሪ አውሬ

    ዳን 7:7

ተጨማሪ ጥያቄ፦

ዳንኤል 7:8, 24 ፍጻሜውን ያገኘው እንዴት ነው?

ዓይኖችና አፍ ያለው አንድ ትንሽ ቀንድ ከአሥሩ ቀንዶች መካከል ወጣ፤ ከዚያም ሦስቱን ቀንዶች ነቃቀላቸው

በቀጣይ ጥናትህ ላይ፦

በራእይ ምዕራፍ 13 ላይ የተገለጹት አውሬዎች እነማንን ይወክላሉ?

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ