ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት | ዘፍጥረት 42–43
ዮሴፍ እጅግ ፈታኝ በሆነ ሁኔታ ውስጥ ራሱን ገዝቷል
ዮሴፍ ባልጠበቀው ሁኔታ ከወንድሞቹ ጋር ፊት ለፊት በተገናኘበት ወቅት ምን ዓይነት የተደበላለቀ ስሜት ተሰምቶት ሊሆን እንደሚችል እስቲ አስቡት። ዮሴፍ ወዲያውኑ ለወንድሞቹ ማንነቱን ከገለጠላቸው በኋላ አቅፎ ሊስማቸው አሊያም ደግሞ የበቀል እርምጃ ሊወስድባቸው ይችል ነበር። ሆኖም ዮሴፍ በስሜት ተገፋፍቶ የሆነ ነገር ከማድረግ ተቆጥቧል። እናንተስ የቤተሰባችሁ አባላት ወይም ሌሎች ሰዎች ኢፍትሐዊ ድርጊት ቢፈጽሙባችሁ ምን ታደርጋላችሁ? ዮሴፍ የተወው ምሳሌ ተንኮለኛ የሆነውን ልባችንን ከመከተልና በስሜታዊነት እርምጃ ከመውሰድ ይልቅ ራሳችንን መግዛታችንና መረጋጋታችን ምን ያህል ጠቃሚ እንደሆነ ያስተምረናል።
የዮሴፍን ምሳሌ መከተል የምትችልባቸው አንዳንድ አቅጣጫዎች የትኞቹ ናቸው?