ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት | ዘፀአት 1–3
“መሆን የምፈልገውን እሆናለሁ”
ይሖዋ የማንነቱን አንድ አስገራሚ ገጽታ ለሙሴ ገልጾለታል። ይሖዋ በእያንዳንዱ ሁኔታ ዓላማውን ለመፈጸም መሆን የሚያስፈልገውን ሁሉ ይሆናል፤ ሆኖም ይህን የሚያደርገው ፍጹም የሆኑትን መሥፈርቶቹን በማይጥስ መንገድ ነው። ወላጆች ልጆቻቸውን ለመንከባከብ ሲሉ የተለያዩ የሥራ ድርሻዎችን እንደሚወጡ ሁሉ ይሖዋም ልጆቹን ለመንከባከብ ሲል መሆን የሚያስፈልገውን ሁሉ ይሆናል።
ይሖዋ እኔን ለመርዳት ሲል መሆን የሚያስፈልገውን ሁሉ የሆነው እንዴት ነው?