የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w22 የካቲት ገጽ 31
  • ይህን ያውቁ ኖሯል?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ይህን ያውቁ ኖሯል?
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2022
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ይሖዋ የአቅማችንን ውስንነት ግምት ውስጥ ያስገባል
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2009
  • ይህን ያውቁ ኖሯል?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2017
  • አምላክን የሚያስደስት መሥዋዕት ማቅረብ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2007
  • ወፎች ከሕንፃዎች ጋር ሲጋጩ
    ንቁ!—2009
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2022
w22 የካቲት ገጽ 31

ይህን ያውቁ ኖሯል?

እስራኤላውያን ዋኖሶችንም ሆነ ርግቦችን መሥዋዕት አድርገው እንዲያቀርቡ የተፈቀደላቸው መሆኑ ጠቃሚ የነበረው ለምንድን ነው?

በሕጉ መሠረት ዋኖሶችም ሆኑ ርግቦች ለይሖዋ መሥዋዕት ሆነው መቅረብ ይችሉ ነበር። ስለ መሥዋዕት በሚገልጹት ሕጎች ላይ እነዚህ ሁለት ወፎች ሁልጊዜ አብረው ይጠቀሳሉ፤ አንዳቸውን በሌላኛቸው ፋንታ ማቅረብም ተፈቅዷል። (ዘሌ. 1:14፤ 12:8፤ 14:30) ይህ መሆኑ እስራኤላውያንን ይጠቅማቸው የነበረው ለምንድን ነው? አንደኛ፣ ዋኖሶችን በቀላሉ ማግኘት የማይቻልባቸው ጊዜያት ነበሩ። ለምን?

ዋኖስ

ዋኖሶች ከቦታ ወደ ቦታ የሚፈልሱ ወፎች ናቸው፤ እስራኤል ውስጥ የሚገኙት በሞቃት ወራት ነው። በየዓመቱ ጥቅምት ላይ ሞቅ ያለ አየር ፍለጋ ወደ ደቡብ ይፈልሳሉ፤ በጸደይ ወቅት ደግሞ ወደ እስራኤል ምድር ይመለሳሉ። (መኃ. 2:11, 12፤ ኤር. 8:7) በመሆኑም በጥንቷ እስራኤል በክረምት ወቅት ለመሥዋዕት የሚሆኑ ዋኖሶችን ማግኘት አስቸጋሪ ነበር።

ርግብ

በሌላ በኩል ግን ርግቦች በአብዛኛው ወደ ሌላ አካባቢ አይፈልሱም፤ በመሆኑም በእስራኤል ምድር ዓመቱን ሙሉ ይገኙ ነበር። በተጨማሪም ርግቦችን ቤት ውስጥ ማርባት የተለመደ ነበር። (ከዮሐንስ 2:14, 16 ጋር አወዳድር።) ባይብል ፕላንትስ ኤንድ አኒማልስ የተባለው መጽሐፍ እንዲህ ይላል፦ “በፓለስቲና በነበሩ መንደሮችና ትናንሽ ከተሞች በሙሉ ርግቦችን ማርባት የተለመደ ነበር። እያንዳንዱ አባወራ ግድግዳው ላይ ቀዳዳ በማበጀት ለርግቦቹ ጎጆ ይሠራ ነበር።”—ከኢሳይያስ 60:8 ጋር አወዳድር።

ጎጆ ውስጥ ያለች ርግብ

ይሖዋ በእስራኤል ውስጥ ዓመቱን ሙሉ የሚገኙ ወፎች መሥዋዕት ሆነው እንዲቀርቡ መፍቀዱ አፍቃሪ እና ምክንያታዊ እንደሆነ ያሳያል።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ