የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • g95 1/8 ገጽ 3-4
  • ሴቶች በአሁኑ ጊዜ ይከበራሉን?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ሴቶች በአሁኑ ጊዜ ይከበራሉን?
  • ንቁ!—1995
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • የአንድ ሕፃን ወንድ ወይም ሴት መሆን የሚወሰነው እንዴት ነው?
  • ከፍተኛ መጠን ያለው አሳዛኝ ሁኔታ
  • ሴቶች፣ በቤታቸው ውስጥ ይከበራሉን?
    ንቁ!—1995
  • አምላክ ሴቶችን በአክብሮትና በአሳቢነት ይይዛቸዋል
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2012
  • አምላክ በእርግጥ ለሴቶች ያስብላቸዋል?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2012
  • ‘በጌታ ሥራ የሚደክሙ’ ሴቶች
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1991
ለተጨማሪ መረጃ
ንቁ!—1995
g95 1/8 ገጽ 3-4

ሴቶች በአሁኑ ጊዜ ይከበራሉን?

አንዳንድ በነገሩ የተገረሙ ወንዶች እስከነአካቴው ይህ ጥያቄ ለምን ይነሳል? ሊሉ ይችላሉ። ይሁን እንጂ ሴቶች በታሪክ ዘመናት በሙሉና በዚህ በዛሬው ዓለም የደረሰባቸውን ነገር ስንመረምር የሚከተሉት ጥቂት ጥያቄዎች የዚህን መልስ ይጠቁሙናል።

በሰው ልጆች የእርስ በርስ ግንኙነት በዋነኛነት ጨቋኞችና ተጨቋኞች የነበሩት እነማን ናቸው? በጋብቻ ግንኙነት ውስጥ በአብዛኛው ድብደባና ሥቃይ የደረሰባቸው እነማን ናቸው? ወንዶች ናቸው ወይስ ሴቶች? በሰላም ዓመታትም ሆነ በጦርነት ወቅቶች ተገድደው የተደፈሩት እነማን ናቸው? በልጅነታቸው ተገደው በሩካቤ ሥጋ የተደፈሩት በአብዛኛው እነማን ናቸው? ወንዶች ልጆች ናቸው ወይስ ልጃገረዶች? አብዛኛውን ጊዜ ወንዶች ባወጧቸው ድንጋጌዎች በሁለተኛ ደረጃ ዜግነት ተወስነው እንዲኖሩ የተፈረደባቸው እነማን ናቸው? የመምረጥ ነጻነት ተነፍጓቸው የኖሩት እነማን ናቸው? የትምህርት ዕድላቸው በአብዛኛው ተገድቦባቸው የኖሩት እነማን ናቸው? ወንዶች ናቸው ወይስ ሴቶች?

እነዚህን የመሳሰሉ በርካታ ጥያቄዎችን መጠየቅ ቢቻልም ሐቁ ግልጽ ነው። ኤልዛቤት ቡሚለር ሜይ ዩ ቢ ዘ ማዘር ኦቭ ኤ ሃንድረድ ሳንስ (የመቶ ወንድ ልጆች እናት ያድርጋችሁ) በተባለውና በሕንድ አገር ያጋጠማቸውን ሁኔታ መሠረት በማድረግ በጻፉት መጽሐፋቸው እንዲህ ሲሉ ጽፈዋል:- “አራት መቶ ሚልዮን ከሚያክሉት የሕንድ ሴቶችና ሴት ልጆች 75 በመቶ የሚሆነውን ክፍል የምትወክለው ተራዋ የሕንድ ሴት የምትኖረው በገጠር መንደሮች ነው። . . . ፍላጎት ቢኖራትም ማንበብም ሆነ መጻፍ አትችልም። ከተወለደችበት አካባቢ ከሠላሳ ኪሎ ሜትር በላይ ተጉዛ አታውቅም።” ይህ እኩል የትምህርት አጋጣሚ ያለማግኘት ችግር በሕንድ አገር ብቻ ሳይሆን በመላው ዓለም የተስፋፋ ችግር ነው።

በጃፓን አገርም እንደ ብዙዎቹ ሌሎች አገሮች የትምህርት ዕድል ባገኙ ወንዶችና ሴቶች መካከል ጎላ ያለ ልዩነት አለ። የ1991 ዘ አሳሂ ይርቡክ እንደሚለው አራት ዓመት በሚፈጁ የዩኒቨርሲቲ ኮርሶች የሚካፈሉ ወንድ ተማሪዎች ቁጥር 1,460,000 ሲሆን የሴቶቹ ቁጥር ግን 600,000 ብቻ ነው። በመላው ዓለም የሚኖሩ ሴቶች በትምህርት መስክ ከወንዶች ጋር እኩል አጋጣሚ እንዳልተሰጣቸው የሚያረጋግጥ ማስረጃ ሊያቀርቡ እንደሚችሉ አያጠራጥርም። ‘ትምህርት ለወንዶች ብቻ ነው’ የሚል ዝንባሌ ከፊታቸው ተጋርጦባቸው ኖሯል።

ሱዛን ፋሉዲ በቅርቡ ባሳተሙት ባክላሽ፣ ዘ አንዲክለርድ ዋር አጌንስት አሜሪካን ዉሜን (በቀል፣ በአሜሪካ ሴቶች ላይ የሚካሄደው ያልታወጀ ጦርነት) በተባለው መጽሐፋቸው ሴቶች በዩናይትድ ስቴትስ ስላላቸው የኑሮ ደረጃ የሚከተሉትን ተገቢ ጥያቄዎች ጠይቀዋል። “የአሜሪካ ሴቶች ከወንዶች ጋር እኩል ከሆኑ በድህነት ከሚኖሩ ሰዎች በሙሉ ሁለት ሦስተኛ የሚሆኑት ሴቶች የሆኑት ለምንድን ነው? . . . ከወንዶች ይበልጥ በጎስቋላ ጎጆዎች ውስጥ የሚኖሩት፣ የሕክምና ዋስትና ለማግኘት የማይችሉት፣ የጡረታ መብት ባለማግኘት ረገድ ከወንዶች በእጥፍ የሚበልጡት ለምንድን ነው?”

በእርግጥም አብዛኛው ሥቃይ የወረደው በሴቶች ላይ ነው። ከወንዶች የሚደርስባቸውን ውርደት፣ ስድብ፣ ወሲባዊ ጥቃትና ንቀት ለመሸከም ተገደዋል። ይህ ግፍ ባልበለጸጉ አገሮች ብቻ የተወሰነ አይደለም። የዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት የፍርድ ኮሚቴ በሴቶች ላይ ስለሚፈጸም የጉልበት ጥቃት አንድ ሪፖርት አውጥቷል። ሪፖርቱ በጣም አስደንጋጭ የሆኑ ሐቆችን አጋልጧል። “በየስድስት ደቂቃ አንዲት ሴት ተገድዳ ትደፈራለች፣ በየአሥራ አምስት ሴኮንዱ አንዲት ሴት ትደበደባለች። . . . በዚህ አገር በጉልበት ለሚፈጸም ወንጀል ከመጋለጥ ነጻ የሆነች ሴት የለችም። በአሁኑ ጊዜ በሕይወት ከሚኖሩ አራት አሜሪካውያን ሴቶች መካከል ሦስቱ ቢያንስ አንድ ጊዜ በጉልበት የሚፈጸም ወንጀል ተጠቂዎች ይሆናሉ።” በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ከሦስት እስከ አራት ሚልዮን የሚደርሱ ሴቶች ከባሎቻቸው የጉልበት ጥቃት ይደርስባቸዋል። በ1990 በሴቶች ላይ የሚፈጸመውን ጥቃት ለመከላከል የወጣ ደንብ የተደነገገው በዚህ አሳዛኝ ሁኔታ ምክንያት ነው።— የምክር ቤት ሪፖርት፣ ዘ ቫዮለንስ አጌንስት ዉሜን አክት ኦቭ 1990

አሁን ሴቶች በመላው ዓለም በሚኖሩ ወንዶች የተዋረዱባቸውንና አክብሮት የጎደላቸው ድርጊቶች የተፈጸሙባቸውን አንዳንድ ሁኔታዎች እንመርምር። ከዚያ በኋላ በመጨረሻዎቹ ሁለት ርዕሶች ወንዶችም ሆኑ ሴቶች በሁሉም የኑሮ መስኮች እንዴት እርስ በርስ ሊከባበሩ እንደሚችሉ እንመለከታለን።

የአንድ ሕፃን ወንድ ወይም ሴት መሆን የሚወሰነው እንዴት ነው?

“የአንድ ያልተወለደ ሕፃን ወንድ ወይም ሴት መሆን የሚወሰነው ሽሉ በተፀነሰበት ጊዜ ሲሆን በዚህ ረገድ ወሳኝ ሚና ያለው የወንዱ ዘር ሕዋስ ነው። አንዲት ሴት የምታፈራው እንቁላል በሙሉ ኤክስ ወይም ሴቴ ክሮሞዘም ያለው በመሆኑ ሴት ነው። የወንዱ ዘር ሕዋሶች ግን ገሚሶቹ ኤክስ ክሮሞዞም ያላቸው ሲሆኑ ገሚሶቹ ዋይ ወይም ወንዴ ክሮሞዞም ያላቸው ናቸው።” ስለዚህ ሁለት ኤክስ ክሮሞዞሞች በሚጣመሩበት ጊዜ ሴት ልጅ ስትፀነስ ወንዴው ዋይ ከሴቴው ኤክስ ክሮሞዞም ጋር በሚጣመርበት ጊዜ ወንድ ልጅ ይፀነሳል። በዚህ ምክንያት አንዲት ሴት ወንድ ወይም ሴት ልጅ መውለድዋ የሚወሰነው በወንዴው ዘር ውስጥ በሚገኘው ክሮሞዞም ነው። (ኤቢሲስ ኦቭ ዘ ሂውማን ቦዲ፣ የሪደርስ ዳይጀስት ጽሑፍ) አንድ ባል ሚስቱን ለምን ሴት ልጅ ብቻ ትወልጃለሽ ብሎ የሚያማርርበት ምንም ምክንያት የለውም። የመራባት ሎተሪ ውጤት በመሆኑ ማንም ማንንም ሊያማርር አይችልም።

ከፍተኛ መጠን ያለው አሳዛኝ ሁኔታ

ኤልዛቤት ፎክስ ጀኖቨዝ ፌሚኒዝም ዊዝአውት ኢሉዥንስ በተባለው መጽሐፋቸው እንደሚከተለው ሲሉ ጽፈዋል:- “ብዙ ወንዶች . . . እየጨመረ በሚሄድ መጠን ጉልበታቸውን አሁንም የበላይነት በሚያሰጣቸው አንድ ሁኔታ፣ ማለትም ከሴቶች ጋር ባላቸው ግንኙነት ለመጠቀም እንደሚፈተኑ የምናምንበት በቂ ምክንያት አለን። በዚህ ረገድ ያለኝ ጥርጣሬ ትክክል ከሆነ እጅግ አሳዛኝ የሆነ ሁኔታ ከፊታችን ተደቅኗል ማለት ነው።” ይህ እጅግ አሳዛኝ ሁኔታ እብሪተኛ ከሆነ ባል፣ አባት ወይም “የእኩልነትንና የፍትሕን ፈተና” ማለፍ ከተሳነው ከማንኛውም ወንድ በየዕለቱ ሥቃይ የሚቀበሉትን በሚልዮን የሚቆጠሩ ሴቶች ይነካል።

“አሁንም [በዩናይትድ ስቴትስ በሚገኙ] ሠላሳ ክፍለ አገሮች ባሎች ሚስቶቻቸውን አስገድደው የጾታ ግንኙነት እንዲፈጽሙ ሕግ ይፈቅድላቸዋል። በቤት ውስጥ ጠብ የሚፈጥሩ ወንዶች እንዲታሠሩ የሚያስገድድ ሕግ ያላቸው ክፍለ አገሮች አሥር ብቻ ናቸው። . . . ቤታቸውን ለቅቀው ከመውጣት ሌላ ምንም የተሻለ አማራጭ ያላገኙ ሴቶችም ቢሆኑ ይህን አማራጭ ጥሩ አማራጭ ሆኖ አላገኙትም። . . . በየዓመቱ በደረሰባቸው ድብደባ ምክንያት ከቤታቸው ከሚሸሹት 1 ሚልዮን የሚያክሉ ሴቶች መካከል አንድ ሦስተኛ የሚያክሉት ምንም ዓይነት መጠለያ ለማግኘት አልቻሉም።”— ባክላሽ፣ ዘ አንዲክለርድ ዋር አጌንስት አሜሪካን ዉሜን የተባለው መጽሐፍ መግቢያ፣ በሱዛን ፋሉዲ የተደረሰ።

በሚልዮን ለሚቆጠሩ ሰዎች በቤተሰብ ክልል ውስጥ የሚነሳ ጠብ የቤተሰብ ኑሮ ጥቁር ገጽታ ሆኖባቸዋል

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ