የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • g95 4/8 ገጽ 28-29
  • የመጽሐፍ ቅዱስ አመለካከት

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የመጽሐፍ ቅዱስ አመለካከት
  • ንቁ!—1995
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ሰዎች ቁማር የሚጫወቱት ለምንድን ነው?
  • የአምላክ አመለካከት
  • ቁማር መጫወት ምን ስህተት አለው?
    ንቁ!—2002
  • መጽሐፍ ቅዱስ ቁማርን ያወግዛል?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2011
  • የአንባብያን ጥያቄዎች
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2002
  • በቁማር ወጥመድ ላለመያዝ መጠንቀቅ
    ንቁ!—2002
ለተጨማሪ መረጃ
ንቁ!—1995
g95 4/8 ገጽ 28-29

የመጽሐፍ ቅዱስ አመለካከት

ክርስቲያኖች ቁማር መጫወት ይገባቸዋልን?

ቁማር ከፍተኛ ኪሣራ የሚያስከትል ልማድ ነው። አብዛኛውን ጊዜ ከአንድ ሰው ገቢ ከግማሽ የሚበልጠውን የሚያሟጥጥ ከመሆኑም በላይ ከፍተኛ ዕዳ ውስጥ ሊያስገባ ይችላል። ይህ ልማድ ትዳር ሊያፈርስና ከሥራ ሊያስወጣ ከመቻሉም በላይ ወንጀል እስከመፈጸም ሊያደርስ ይችላል። በቁማር ልማድ የተመረዙ ሰዎች በሌላ ዓይነት ሱሶች የተጠመዱ ሰዎች የለመዱትን ሲያጡ የሚሰማቸው መጥፎ ስሜት ሁሉ ይሰማቸዋል።

ቁማር በመላው ዓለም የተስፋፋ በመሆኑ አንዳንድ አገሮች ቁማርን “ብሔራዊ የጊዜ ማሳለፊያ” ብለው እስከ መጥራት ደርሰዋል። ይሁን እንጂ ቁማር ምንድን ነው? ቁማር ዘ ወርልድ ቡክ ኢንሳይክሎፔድያ እንደሚለው “ወደፊት የሚፈጸም ክንውን በሚያስገኘው ውጤት ላይ መወራረድ” ማለት ነው። “ቁማርተኞች ወደፊት ስለሚፈጸም ነገር ሲተነብዩ የተነበዩት ነገር በትክክል ስለመፈጸሙ ገንዘብ ወይም ሌላ ዋጋ ያለው ነገር ያስይዛሉ። ውጤቱ ተረጋግጦ ከታወቀ በኋላ አሸናፊው የተሸናፊውን ገንዘብ ይወስዳል።”

ቁማር አዲስ የተፈጠረ ክስተት አይደለም። በማዕከላዊ አሜሪካ ይኖሩ የነበሩት የጥንቶቹ የማያ ጎሣዎች ፖክታቶክ የተባለ ከፍተኛ ተወዳጅነት የነበረው የኳስ ጨዋታ ነበራቸው። ይህን ጨዋታ አዝቴኮች ትላችትሊ ብለው ሲጠሩት አሜሪካስ የተባለው መጽሔት እን ደሚለው “አንዳንዶች [በእነዚህ ጨዋታዎች ላይ በመወራረድ] ሀብታቸውን በሙሉ ከስረው የገዛ ሕይወታቸውን እስከ ማጣት ደርሰዋል።” እነዚህ ጥንታውያን ሕዝቦች በውርርዱ ትኩሳት ሲያዙ “አንዲት የምትሽከረከር ኳስ ለምታስገኘው ውጤት መላ ሕይወታቸውን ለባርነት አሳልፎ እስከመስጠት ይደርሱ ነበር።”

ብዙዎች በውርርድ ትኩሳት ይሸነፉ የነበረው ለምንድን ነው? በዩናይትድ ስቴትስ የሕዝባዊ ጨዋታዎች ምርምር ተቋም ፕሬዘዳንት የሆኑት ዱዋን ቡርክ እንደሚሉት “ቁጥራቸው እየጨመረ የሚሄድ ብዙ ሰዎች ቁማርን ተቀባይነት እንዳለው የጊዜ ማሳለፊያ መቁጠር በመጀመራቸው ነው።” አንዳንድ ሃይማኖታዊ ድርጅቶችም እንኳ ቁማርን እንደ ጥሩ ገንዘብ ማግኛ መቁጠር ጀምረዋል።

ቁማር በጣም የተለመደና የረዥም ዘመን ታሪክ ያለው ይሁን እንጂ ለክርስቲያኖች ምንም ጉዳት የሌለው ጊዜ ማሳለፊያ ሊሆን ይችላልን? ወይስ የሚያስከትለው ጉዳት አለ?

ሰዎች ቁማር የሚጫወቱት ለምንድን ነው?

በአጭሩ ለማሸነፍ ሲሉ ነው። ለቁማርተኞች ቁማር ብዙ ጥረትና ድካም ሳያስፈልግ በቀላሉና በፍጥነት ገንዘብ የሚገኝበት ዘዴ መስሎ ይታያቸዋል። ብዙ ጊዜያቸውን “በአሸናፊነት” ስለሚያገኙት ገንዘብና ገንዘቡ ስለሚያስገኝላቸው ዝናና ዕቃ በማለም ያሳልፋሉ።

ይሁን እንጂ ቁማርተኛው ለማሸነፍ ያለው ዕድል በጣም አነስተኛ ነው። ለምሳሌ ያህል የስታትስቲክስ ሊቅ የሆኑት ራልፍ ሊሽ በጀርመን አገር “በጀርመን የሎተሪ ዕጣዎች ከማሸነፍ ይልቅ በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ በመብረቅ የመመታታችሁ አጋጣሚ በአራት እጥፍ ይበልጣል” ብለዋል። ይህን ለማመን አስቸጋሪ ሆኖ ካገኛችሁት ደግሞ “ወንዶች ከሆናችሁ እስከ 100 ዓመት ዕድሜ የመድረስ ዕድላችሁ የሎተሪ ዕጣ ከማሸነፍ 7,000 ጊዜ ይበልጣል።” የሚያስገርመው ግን ቁማርተኛው ይህን አሳምሮ ያውቃል። ታዲያ በቁማሩ እንዲቀጥል የሚገፋፋው ነገር ምንድን ነው?

ዶክተር ሮበርት ከስተር ዌን ላክ ራንስ አውት በተባለው መጽሐፋቸው እንደገለጹት ቁማር ለሚጫወቱ አንዳንድ ሰዎች “የሚገኘው የገንዘብ ትርፍ አሸናፊነት የሚያስገኘው አንድ ክፍል ብቻ ነው። . . . ለእነርሱ በጣም አስፈላጊ የሆነው ነገር ገንዘቡን ማግኘት የሚያስገኘው ቅንዓት፣ አክብሮት፣ አድናቆትና ሙገሳ ነው።” ለእነርሱ ትልቁ ነገር “የገንዘብ ረብጣ መሸከምና ‘ይህን ያህል ገንዘብ ያገኘሁ ሰው ነኝ’ ብሎ መኩራራት ነው” በማለት አክለው ጽፈዋል።

በሌላው በኩል ደግሞ ለብዙ ቁማርተኞች ማሸነፍና ማሸነፍ የሚያስገኘው ደስታ ብቻ አይበቃቸውም። ቁማር እንዲጫወቱ የሚገፋፋቸው ስሜት በጣም ኃይለኛ ስለሚሆን የቁማር ሱሰኞች ይሆናሉ። ዶክተር ከስተር በቁማርተኞች ማኅበር አባላት ላይ ባደረጉት ጥናት ላይ ጥናት ከተደረገባቸው ሰዎች 75 በመቶ የሚያክሉት በሚሸነፉበት ጊዜ እንኳን አሸንፌአለሁ! እያሉ ጉራ እንደሚነዙ ተናግረዋል። አዎን፣ ቁማር የአልኮልም ሆነ የሌላ አደንዛዥ ዕፅ ሱስ ከሚያስከትለው ጉዳት ያላነሰ ጉዳት የሚያስከትል ሱስ ሊሆን ይችላል። በጣም ቀጭን የሆነውን የጊዜ ማሳለፊያ ድንበር ተሻግረው ሱሰኞች የሆኑ ቁማርተኞች ቁጥር ምን ያህል የበዛ ነው? ሱሰኛ ሆነው ገና ሱሰኛነታቸውን ያላወቁትስ ምን ያህል ብዙ ናቸው?

የአምላክ አመለካከት

መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ቁማር በሰፊው አያብራራም። ቢሆንም አምላክ ቁማርን እንዴት እንደሚመለከት እንድናውቅ የሚያስችሉንን መሠረታዊ ሥርዓቶች ይገልጽልናል።

ቁማር የስግብግብነት መንፈስን እንደሚያንጸባርቅ ከተሞክሮ መገንዘብ ተችሏል። መጽሐፍ ቅዱስ ‘ማንኛውም ስግብግብ ሰው የአምላክን መንግሥት እንደማይወርስ’ በመናገር ስግብግብነትን አጥብቆ ያወግዛል። (ኤፌሶን 5:5) ቁማርተኞች በሚሸነፉበት ጊዜ እንኳን ስግብግብነታቸው በግልጽ ይታያል። አንድ ባለሥልጣን እንደተናገሩት ቁማርተኛው “በበለጠ ብዙ ገንዘብ በመወራረድ የከሰረውን ገንዘብ መልሶ ለማግኘት ይሞክራል። ብዙ ገንዘብ ካሸነፈ ያሸነፈውን በሙሉ እስኪያጣ ድረስ የውርርዱን ገንዘብ ይጨምራል።” አዎን፣ በእርግጥም ስግብግብነት የቁማር ክፍል ነው።

አንዳንዶች የትልቅነት ስሜት እንዲሰማቸው ሲሉ ቁማር ይጫወታሉ። በሱሰኛ ቁማርተኞች ላይ የተደረገ አንድ ጥናት እንደሚያመለክተው 94 በመቶ የሚያክሉት ቁማር “የትልቅነት ስሜት እንዲሰማ የሚያደርግ ድርጊት” እንደሆነ ሲናገሩ 92 በመቶ የሚያክሉት ደግሞ ቁማር በሚጫወቱበት ጊዜ “ትልቅ ሰው” እንደሆኑ እንደሚሰማቸው ተናግረዋል። አምላክ ግን “ትዕቢትንና እብሪትን . . . እጠላለሁ” ብሏል። በዚህም ምክንያት ክርስቲያኖች ልከኝነትንና ትሕትናን እንዲኮተኩቱ ማሳሰቢያ ተሰጥቷቸዋል።— ምሳሌ 8:13፤ 22:4፤ ሚክያስ 6:8

በተጨማሪም ቁማር አለ ብዙ ድካምና ውጣ ውረድ ገንዘብ ሊያስገኝ የሚችል ዘዴ መስሎ ስለሚታይ ስንፍናን ያስፋፋል። የአምላክ ቃል ግን ክርስቲያኖች ተግተው እንዲሠሩ በግልጽ ይመክራል።— ኤፌሶን 4:28

ከዚህም በላይ አንዳንድ ቁማርተኞች ዕድል ወይም ዕጣ ለሚሉት ነገር ከፍተኛ ቦታ ስለሚሰጡ የዕድል አምላኪዎች ይሆናሉ። ይህም መጽሐፍ ቅዱስ “ዕድል ለተባለ ጣዖት” ማዕድ ስላዘጋጁ ሰዎች ከተናገረው ጋር ይመሳሰላል። እነዚህ ሰዎች ጣዖት አምላኪዎች በመሆናቸው “ለመታረድ” ተዳርገዋል።— ኢሳይያስ 65:11, 12

አንድ ሰው የሎተሪ ቲኬት ወይም ቁማር የሚጫወትበት ገንዘብ በነፃ ቢሰጠውስ? እንዲህ ያለውን ስጦታ መቀበል ከአምላካዊ መሠረተ ሥርዓቶች የራቀውን የቁማር ሥራ መደገፍ ይሆናል።

የለም፣ ክርስቲያኖች ቁማር መጫወት አይገባቸውም። የአንድ መጽሔት አዘጋጅ እንዳለው ‘ቁማር ስህተት ከመሆኑም በላይ አክሳሪ ነው።’

[በገጽ 28 ላይ የሚገኝ ምንጭ]

Valentin/The Cheaters, Giraudon/Art Resource

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ