የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • g97 4/8 ገጽ 25
  • የፍጥነት ንጉሥ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የፍጥነት ንጉሥ
  • ንቁ!—1997
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • “ግሩምና ድንቅ” ሆነህ ተፈጥረሃል!
    ንቁ!—2011
  • እንስሳት ልጆቻቸውን የሚመግቡበትና የሚያሠለጥኑበት መንገድ
    ንቁ!—2005
  • የዱር እንስሳት ቋንቋ—የእንስሳት ቋንቋ ምሥጢሮች
    ንቁ!—2002
  • ታላቁ ፍልሰት
    ንቁ!—2003
ንቁ!—1997
g97 4/8 ገጽ 25

የፍጥነት ንጉሥ

በደቡብ አፍሪካ የንቁ! መጽሔት ዘጋቢ እንዳጠናቀረው

ይህ የማዕረግ ስም የተሰጠው ለማን ነው? በአጭር ርቀት በሩጫ ፍጥነት ከዓለም አንደኛ ለሆነው ለአቦሸማኔ ወይም ለቺታ ነው። የአንዱ አቦሸማኔ ቡራቡሬነት ከሌላው አይመሳሰልም። ቺታ የሚል ስያሜ የተሰጠውም በዚህ ምክንያት ነው ይባላል። ቺታ የሚለው ቃል ከሳንስክሪት ቋንቋ የተገኘ ሲሆን ትርጉሙም “ነጠብጣብ ያለው አካል” ማለት ነው።

አንዳንዶች እንደሚሉት ይህ የድመት ዝርያ በመጀመሪያ ሲታይ ከእግር በቀር ሌላ ሰውነት ያለው አይመስልም። ሌሎች ደግሞ ወገቡ ጎበጥ ያለና ጭንቅላቱም በጣም ትንሽ እንደሆነ ይናገራሉ። ይሁን እንጂ አቦሸማኔ የተለየ ችሎታ እንዲኖረው ያስቻሉት እነዚህ ልዩ ገጽታዎቹ ናቸው። የኋላ እግሮቹ ረዣዥሞች መሆናቸው ሲራመድና ሲሮጥ ግርማ ሞገስ እንዲኖረው አስችለውታል። ይህ አውሬ በእርግጥም በጣም ፈጣን ሯጭ ነው! አንዱ አቦሸማኔ በሰዓት 110 ኪሎ ሜትር ሊሮጥ ይችላል።

የአቦሸማኔ አፈጣጠር ለፈጣን ሩጫ የሚያመች ነው። ቀላል ክብደት ካላቸው አጥንቶቹ መካከል እንደልቡ የሚተጣጠፈውና እንደሞላ መለጠጥና ማጠር የሚችለው የጀርባ አጥንት ይገኛል። በተጨማሪም አቦሸማኔ ሰፊ ደረት፣ ትልቅ ሳንባ፣ ጠንካራ ልብ፣ ሚዛኑን እንዲጠብቅ የሚያስችለው ጅራትና በፍጥነት እንዲተነፍስ የሚያስችለው ሰፊ አፍንጫ አለው። ይህ ሁሉ ለዚህ አውሬ ፈጣን ሯጭነት አስተዋጽኦ ያደርጋል። ይሁን እንጂ የአቦሸማኔ ፍጥነት ለረዥም ጊዜ አይቆይም። በከፍተኛ ፍጥነት 400 ሜትር ያህል ከሮጠ በኋላ ቆም ብሎ አረፍ ማለት ይኖርበታል።

አብዛኛውን ጊዜ አቦሸማኔዎች በሰዎች ላይ የሚያደርሱት ጉዳት የለም። ለበርካታ ዘመናት አቦሸማኔዎችን ሲያረቡ የኖሩት ቫን ዳይክ ዘ ቺታስ ኦቭ ደ ቪልት በተባለው መጽሐፋቸው ላይ እንዲህ ብለዋል:- “ተመግበው ካበቁ በኋላና ከመጨለሙ በፊት ያሉትን ጥቂት ጊዜያት ቤተሰቦች ከሆኑት የድመት ዘሮች ጋር ማሳለፍ ያስደስተኛል። በመካከላችን የመተማመን መንፈስ ስለዳበረ ለማዳ ባይሆኑም ምንም ዓይነት ጉዳት እንደማያደርሱብኝ አውቃለሁ።”

የሰው ልጆች ግን ለአቦሸማኔዎች አልተኙላቸውም። ለምሳሌ ያህል በአፍሪካ የሚገኙ አዳኞች ለቆዳቸው ሲሉ ከመግደላቸውም በላይ መኖሪያቸው በሰዎች በመወሰዱ የመሮጫ ሥፍራቸው ጠቦባቸዋል። በዚህም ምክንያት የአቦሸማኔዎች ብዛት በእጅጉ ተመናምኗል። በአንድ ወቅት በሕንድ አገር በብዛት ይታዩ የነበሩት አቦሸማኔዎች ከ1952 ወዲህ ከአገሪቱ ጠፍተዋል። በተጨማሪም የምሥራቃዊ ሜዲትራንያን አዋሳኝ በሆኑ አገሮች በአሁኑ ወቅት አይገኙም።

በአምላክ አዲስ ዓለም ውስጥ የአራዊትና የእንስሳት ሕልውና ስግብግብ በሆኑ ሰዎች አደጋ ላይ እንደማይወድቅ ማወቃችን ምንኛ የሚያስደስት ነው! (ኢሳይያስ 11:6-9) ምናልባት በዚያ ጊዜ ይህን ድንቅ ተፈጥሮ ያለውን የፍጥነት ንጉሥ የማየት መብት ታገኝ ይሆናል።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ