የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • g01 6/8 ገጽ 22
  • አትክልቶችን ተመገብ!

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • አትክልቶችን ተመገብ!
  • ንቁ!—2001
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • የተመጣጠነ ምግብ ማግኘት ይቻላል
    ንቁ!—2002
  • 1ኛው ቁልፍ​—ጥሩ አመጋገብ ይኑርህ
    ንቁ!—2011
  • ለምግብ ደህንነትና ለጤናማ አመጋገብ ወሳኝ የሆኑ ሰባት ነገሮች
    ተጨማሪ ርዕሰ ጉዳዮች
  • ሥር የሰደዱ መንስኤዎችና ዘላቂ መዘዞች
    ንቁ!—2003
ንቁ!—2001
g01 6/8 ገጽ 22

አትክልቶችን ተመገብ!

ብራዚል የሚገኘው የንቁ! ዘጋቢ እንደጻፈው

“ይመርራሉ።” “አይጣፍጡም።” “በልቻቸው አላውቅም።”

እነዚህ አባባሎች ብዙ ሰዎች አትክልቶችን ላለመመገብ ከሚደረድሯቸው ሰበቦች ውስጥ ጥቂቶቹ ናቸው። አንተስ? በየቀኑ አትክልት ትመገባለህ? ንቁ! አንዳንዶች አትክልት መመገብ የሚወዱበትን ሌሎች ደግሞ የማይወዱበትን ምክንያት ለማወቅ ቃለ መጠይቆችን አድርጎ ነበር።

አትክልት መመገብ የሚወዱት ወላጆቻቸው አትክልት፣ ጥራጥሬና ፍራፍሬ የመመገብን አስፈላጊነት እንዳስተማሩዋቸው ተናግረዋል። ከዚህ በተቃራኒው ግን አትክልት መመገብ የማይወዱት በልጅነታቸው አትክልት የመመገብ ልማድ እንዳልነበራቸው ተናግረዋል። ከዚህ ይልቅ ኃይል ከመስጠት ያለፈ ጥቅም የሌላቸውን ምግቦች መመገብን ይመርጣሉ። ያም ሆኖ ለጥሩ ጤንነት አትክልቶችን መመገብ አስፈላጊ መሆኑን አይክዱም።

ወላጆች፣ ልጆቻችሁ አትክልቶችን እንዲመገቡ አስተምሯቸው! እንዴት? በተባበሩት መንግሥታት የሕፃናት መርጃ ድርጅት የታተመው ፋክትስ ፎር ላይፍ የተሰኘው ጽሑፍ ከተወለዱ ስድስት ወር አካባቢ የሆናቸው ልጆች ከጡት ወይም በጡጦ ከሚሰጣቸው ወተት በተጨማሪ ተቀቅለው ተልጠውና ተፈጭተው የተዘጋጁ አትክልቶች ቢያንስ በቀን አንዴ ሊሰጣቸው እንደሚገባ ገልጿል። የአትክልቶቹ ዓይነት መብዛት የዚያኑ ያህል ለልጁ ጤንነት ጠቃሚ ነው። ዶክተር ቫግነር ላፖቴ የተባሉ አንድ ብራዚላዊ የሕፃናት ስፔሺያሊስት ለመጀመሪያዎቹ ሁለት ዓመታት ወተት የልጁ ዋነኛ ምግብ ቢሆንም ተጨማሪ ምግቦች መስጠት “ልጁ ከአዳዲስ ጣዕሞች ጋር እንዲተዋወቅ ያደርገዋል” ሲሉ ተናግረዋል።

ካርላ ሊዮኔል ሜዲሲና​—⁠ሚቶስ ኢ ቨርዳዲስ (መድኃኒትን በተመለከተ ያለው አፈ ታሪክና እውነታ) በተባለው መጽሐፋቸው ላይ ትንሽ የብርቱካን ጭማቂ፣ የተፈጩ ፍራፍሬዎች (እንደ ሙዝ፣ ፖም እና ፓፓያ ያሉት)፣ ጥራጥሬና የአትክልት ሾርባ ከላይ ከተገለጸው ጊዜ ቀደም ብሎ ለልጁ መስጠት እንደሚቻል ተናግረዋል። እርግጥ ይህንን በተመለከተ የሚሰጡት አስተያየቶች ስለሚለያዩ አስቀድሞ የሕፃናት ሐኪም ማማከሩ ጥበብ ይሆናል።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ